ስልጠናው የተሰጠው ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት የስፖርት ሳይንስ መምህራን፣ የቀይ መስቀል ክበብ አባላት ተማሪዎች እና የስፖርት ባለሙያዎች ሲሆን ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሃንስ ገብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ሰልጣኞች በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የሚወስዱትን ሰልጠና በሰብዓዊነት እና በመልካም ፍቃደኝነት መርህ የሰውን ልጅ ህይወት ከሞት ከመታደግና እና የአካል ጉዳት እክሎችን ከመቀነስ አንፃር ስልጠናው ትልቅ አስተዋፅዖ ያለው በመሆኑ ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡
የስፖርት ሳይንስ ት/ት ክፍል ኃላፊ እና የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር አብዱላዚዝ ሙሰማ በበኩላቸው እንደገለጹት ይህ ስልጠና ፋይዳው በት/ት ቤት ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎችን ፣ስፖርተኞችን እና ማሕበረሰቡንም ጭምር ከመጥቀም አንፃር ከፍተኛ ድርሻ ያለው መሆኑን አስታውሰው ተጎጂዎች ወደ ጤና ማዕከላት እስኪደርሱ ድረስ ከፍተኛ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ባለሙያዎች ፍፁም በሆነ ሰብዓዊነት ድጋፍ መስጠት እንደሚገባቸውና ስልጠናውም ሰልጣኞችን ለዚህ ብቁ የሚያደርጋቸው መሆኑን በመግለፅ የስልጠናውን ዋና ግብ እና አላማዎችን በዝርዝር ገልጸዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ቀይመስቀል ማሕበር ተወካይ እና አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ሻሚል የሲሩ በበኩላቸው ይህ ስልጠና የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል መርሆዎችን መሰረት በማድረግ የሚሰጥ ፣ ደረጃውን የጠበቀ እና የሙያ እውቅና ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የሚያሰጥ ስልጠና በመሆኑ ሰልጣኞች በትኩረት ስልጠናውን እንዲከታተሉት በማሳሰብ በቀጣይ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር የሚሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለጥበብ እንተጋለን!
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት