ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኢኮቴ ዳይሬክቶሬት

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መማር ማስተማር፣ ምርምር እና ማኅበረሰብ አገልግሎትን ውጤታማ ለማድረግ እና የታሰበውን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የኢኮቴ ሚና ከፍተኛ ነው። በየጊዜው እያደገ የመጣውን የዩኒቨርሲቲውን የተማሪ ቅበላ አቅም በአግባቡ ለማስኬድ እና በተሻለ ጥራት ለማስቀጠል የመረጃ ቴክኖሎጂን በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የተቋቋመበት ዋነኛም ዓላማም ከላይ የተተቀሱትን ዕውን ለማድረግ ነው በዚህም መሠረት ከተቋቋመበት ግዜ ጀምሮም የኔትዎርክ መሠረተ ልማት ዝርጋታን በሰፊው በመሥራት የግቢውን ኔትዎርክ ተደራሽነት የማሳደግ ሥራ በመሥራት ቢሮዎች፣ ቤተ ሙከራዎች እና መማሪያ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ የኔትዎርክ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።

የክፍሉ ተግባር እና ኃላፊነት፦

  • ኢኮቴን በአግባቡ መምራት፣ ማስተዳደር እና የባለሙያዎችን አቅም በተለያዩ ሥልጠናዎች ማሳደግ።
  • የኢኮቴ ፕሮጀክቶችን ፣ የመሠረተ ልማት እና ሲስተሞችን፣ የተቋሙን አሠራር እና የመረጃ አደረጃጀቶችን እን አጠቃላይ አሠራሮችን በኢኮቴ የሚታገዝበትን መንገድ ማቀድ
  • ኢኮቴ የተጠቃሚዎቹን ፍላጎት ተረድቶ በአግባቡ መሟላቱን ማረጋገጥ
  • በፍጥነት እየተለወጠ ያለውን የመረጃ ቴክኖሎጂ ዕድገት በመከታተል በተለይ የዩኒቨርሲቲውን የመማር ማስተማር እና ምርምር ሥራዎችን ሊያግዡ የሚችሉ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን ለዩኒቨርሲቲው አገልግሎት እንዲውሉ ማድረግ።

የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት መዋቅር

የኢኮቴ መዋቅር
የኢኮቴ መዋቅር
Copyright © 2024. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT