ክፍት የሥራ ቦታ

ማስታወቂያ

ለድህረ -ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በድህረ ምርቃ ፕሮግራም በመደበኛውና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ባሉት ፕሮግራሞች አመልካቾችን አወዳድሮ ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

Read more ...

ለነባር የክረምት ትምህርት ተማሪዎች በሙሉ

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በክረምት መርሀ-ግብር ትምህርታችሁን ለምትከታተሉ ነባር

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ሶሲዮሎጂ ፤ ሶሻል አንትሮፖሎጂ እና ሶሻል ወርክ ባለሙያዎች (ESSSWA ) ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 17ኛው ዓመታዊ ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀመረ።

“ውስጣዊ ግጭቶች እና የመቋቋሚያ ስልቶች ( Internal Conflicts and Coping Mechanisms in Ethiopia) ‘’ በሚል ርዕስና በተዛማች ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከቀን 09-10/07/2014 ዓም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ቆይታ የሚያደርገው ይህ 17ኛው ዓመታዊ ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በይፋ ተጀምሯል፡፡

በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል ባስተላለፉት መልዕክት በዓመታዊ ኮንፈረንሱ ለታደሙት ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ ዓመታዊ ኮንፈረንሱ በትክክለኛ ሰዓት ላይ የተካሄደ መሆኑን አስታውሰው በተለይም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በኢትዮጵያ እየተስተዋሉ ያሉትን ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል፤በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመና አገራዊ ምክክር መድረክን የሚመራ አገራዊ ምክክር ኮሚሽንን ለመጀመሪያ ጊዜ ባቋቋመበት ማግስት ይህ ዓመታዊ ኮንፈረንስ መካሄዱ ኮንፈረንሱን ልዩ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ዶክተር ፋሪስ አያይዘውም ሲገልጹ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ምንም እንኳን ከተቋቋመ አስር ዓመት የሞላውና በዕድሜው ብዙም ያልገፋ ተቋም ቢሆንም እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2030 በኢትዮጵያ ከሚገኙ የተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ቀዳሚ ሆኖ ለመገኘት ርዕይ ሰንቆ ተግቶ እየሰራ ያለ ተቋም መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ በተጨማሪም ተቋሙ መሰል ኮንፈረንሶችን የማዘጋጀት አቅሙን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ የመጣ መሆኑን ገልጸው ከዚህ ቀደምም የሚከተሉትን ኮንፈረንሶች 1) Crop Science Society of Ethiopia, 2) Ethiopian Physicists Association Conference, 3) The Grand Celebration of 55th World Theatre Day 4) the 2nd National Research Conference. ያዘጋጀ መሆኑን በማስታወስ ከእነዚህም ልምድ ወስዶ ይህንን ኮንፈረንስ በተሻለ መልኩ ለማዘጋጀት ጥረት ማድረጉን በስፋት አብራርተዋል፡፡

ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ የኢትዮጵያ ሶሲዮሎጂ ፤ ሶሻል አንትሮፖሎጂ እና ሶሻል ወርክ ባለሙያዎች (ESSSWA ) ማህበር ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የአባላቱን ሙያዊ አቅምና ችሎታ በመጠቀም ለሀገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገቶች የበኩሉን ሚና ሲጫወት መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ፕሮፌሰር ጌትነት አያይዘውም ESSSWA በCOVID-19 ወረርሽኝ መከላከል ዙሪያ በተለይም በአዕምሮ ጤንነነትና በስነ ልቡና ድጋፍ ዙሪያ በሀገር ውስጥ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉትና የችግሩ ሰለባ ለሆኑት የማህበረሰብ ክፍሎች ተገቢውን ድጋፍና ስልጠናዎችን በመስጠት የበኩሉን ወገናዊ ሃላፊነት ሲወጣ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ በተጨማሪ ሲገልጹ ESSSWA ከUSAID ጋር በአጋርነት በጋራ እየሰራ መሆኑን ገልጸው Social System Strengthening in Ethiopia (SSSE) የተሰኘውን ፕሮጀክት በ USAID የፋይናንስና ቴክኒካል ድጋፍ እየታገዘ ከቀድሞው Ministry of Labour and Social Affairs (MOLSA) , Ministry of Women , Children , Youth affairs (MoWCYA ), TVET agency እና TVET colleges ጋር በጋራ በመስራት ይህንን ፕሮጀክት በአራት ክልሎች ማለትም በአማራ፤ኦሮሚያ፤ጋምቤላና ደቡብ ክልል ላይ ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ ለወላጅ አልባ ህጻናትና በHIV/AIDS ለተጠቁ ወገኖች ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን በስፋት አብራርተዋል፡፡

የክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶችና የማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትርን መልዕክት በንባብ ያሰሙት ክቡር አቶ ጌታቸው በዳኔ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር “ ውስጣዊ ግጭቶች እና የመቋቋሚያ ስልቶች ( Internal Conflicts and Coping Mechanisms in Ethiopia) ‘ በሚል ለዚህ ዓመታዊ ኮንፈረንስ የተመረጠው ርዕስ በግልጽ የሚያሳየው የESSSWA ማህበርና አባላቱ ለኢትዮጵያ ሰላምና ለህዝቦቿ ደህንነት ያላቸውን ቁርጠኝነትና ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የሚያሳዩትን የሁልጊዜም ዝግጁነት በግልጽ የሚያመላክት መሆኑን ገልጸው ለESSSWA እና ይህንን ዓመታዊ ኮንፈረንስ ላዘጋጁት አካላት ልባዊ ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡

ከመክፈቻ ንግግሩ በኋላ ሁለት ጥናታዊ ጸኁፎች ማለትም “It Only Reopens Old Wounds” Lived Experiences of Amhara Survivors from the Miakadra Massaker in Ethiopia’’ (Adugna Abebe PhD), The Reintegration challenges of internally Displaced Persons by Violent Ethnic Conflict in Dembya Woreda: Nort Western Ethiopia (Getu Ambaye PhD) በሚል የቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ርዕሶች ላይም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ከጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በመገምገም ላይ ይገኛሉ

Read more ...

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የጨቅላ ሕጻናት የእንክብካቤ ማዕከል እና የመምህራን መኖሪያ በሆነው አፓርታማ ግቢ ውስጥ የሚገኘው ሞዴል የማህበረሰብ መድሃኒት ቤት በይፋ ተመረቁ

Read more ...

በ2014 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ለመተግበር በዋቤ ችግኝ ጣቢያ የተዘጋጁት ችግኞችን አስመልክቶ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የስፔሻሊቲ የትምህርት ፕሮግራሞችን መስጠት ጀመረ

Read more ...

We have 326 guests and no members online

Wolkite University, P.O.Box 07, Wolkite, Guragie Zone, SNNPR, Ethiopia | +251-113-220042 | pird@wku.edu.et/president@wku.edu.et

Copyright © 2023. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT