ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 የትምህርት ዘመን ከትምህርት ሚኒስቴር ለማማካሻ ትምህርት (Remedial ) የተመደቡለትን 2778 (ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ስምንት) ተማሪዎችን ጥር 27 እና 28/2016ዓ.ም. እንደሚቀበል አስቀድሞ በመገናኛ ብዙሀን ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡
በዚህ መሰረት ተማሪዎቹ በዛሬው ዕለት ወደ ዩኒቨርሲቲያችን መግባት የጀመሩ ሲሆን በነገው ዕለት ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቀው ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት በነባር ተማሪዎች አማካይነት ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች እጅግ የደመቀ አቀባበል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ውድ ተማሪዎቻችን እንኳን የሰላም አምባሳደር ወደ ሆነው ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና ወደስራ ወዳዱ ማህበረሰብ በሰላም መጣችሁ እያልን ቆይታችሁ ያማረና የሰመረ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን፡፡
ለጥበብ እንተጋለን!
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት