ለዩኒቨርሲቲው የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ፣ ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች በመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ፣ በሰው ሀብት ልማት መመሪያ እና ደንብ ፣ በግዢ ሂደት አፈጻጸም ፣ በንብረት አስተዳደርና በፋይናንስ መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ። ስልጠናውን የሰጡት የሰው ሃብት ልማት ዳይሬክተር ፣ የግዢና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር እና የፋይናንስ ዳይሬክተር ሲሆኑ ሁሉም በየዘርፋቸው ደንብና የአፈጻጸም መመሪያውን በዝርዝር አቅርበዋል:: በቀረበው ደንብና የአፈጻጸም መመሪያ ዙሪያ የስልጠናው ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን በተለይም ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷቸዋል:: በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ኮርፖሬት ማኔጅመንት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር የሻረግ አፈራ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በማጠቃለያ ንግግራቸው ላይ እንደገለጹት መድረኩ መመቻቸቱ በተለይም የጠራ ግንዛቤን እንዲኖር በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸው ገንቢ የሆኑ ሀሳቦች መነሳታቸውን በማስታወስ በቀጣይ ተመሳሳይ የሆነ መድረክ እንደሚኖር ጭምር ገልጸዋል::