የእግር ኳስ የክበባት ውድድር በ12 ቡድኖች እንዲሁም የቅርጫት ኳስ በሶስት ቡድኖች መካከል ለሶስት ሳምንታት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ በቅርጫት ኳሱ ዋርየር፣ መብረቅ እና ማምባ ክበባት የተጋጠሙ ሲሆን በመብረቅ ክበብ አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡ በእግር ኳሱ ውድድሩ በጥሎ ማለፍ አንቲድራግ ክበብ የጸረ-ሙስና ክበብን በማሸነፍ እንዲሁም ሸጋፌስት ክበብ ኢንቫይሮመንታል ክበብን በማሸነፍ ለፍጻሜ ውድድር የበቁ ሲሆን በአንቲድራግ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡
በመዝጊያ ፕሮግራሙ የታደሙት የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ልማት ኮርፖሬት ማኔጅመንት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር የሺሀረግ አፈራ የስፖርታዊ ውድድሩ ዓላማ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ አልባሌ ቦታ ባለመዋል ለመጡለት አላማ ብቻ በመትጋት ጤናማ ሆነው እንዲወጡ ነው ብለዋል። ዶከተር የሺሃረግ አያይዘውም ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ ተማሪዎቹ ላሳዩት ስፖርታዊ ጨዋነት አመስግነዋል።
በመጨረሻም የ2014 ዓ.ም የተማሪዎች ሻምፒዮና ለሆነው የአንቲድራግ የእግር ኳስ ክበብ እና ለመብረቅ የቅርጫት ኳስ ክበብ ሽልማት አበርክተዋል።
በቀጣይም የኮሌጅና የአስተዳደር ቡድኖች ውድድር እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል።