የማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደር ኮ/ማ/ም/ፕ ልዩ ረዳት አቶ ፍቃደ ሲማ በተቋሙ የሚዘጋጀው ይህ አመታዊ የልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድር የተቋሙን ማህበረሰብ የእርስበርስ ግንኙነት ለማጠናከር ፍይዳው የጎላ ነው ብለዋል። አቶ ፍቃደ አክለውሞ ውድድሮቹ ሲካሄዱ ስፖርታዊ ጨዋነት የተሞላባቸው እንዲሆኑ አሳስበዋል።
በእለቱም የዙር ውድድር ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ከ አስተዳደር ሁለት የተጫወተ ሲሆን በኢንጂነሪንግ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል። በሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ ተማሪዎች ዲን ከተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ የተጋጠመ ሲሆን በተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
የልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድሩም በተለያዩ ኮሌጆች፣ በአስተዳደር እንዲሁም በተማሪ ቡድኖች መካከል ከስራ ሰዓት ውጪ እና በእረፍት ቀናት የዙር ውድድር እየተካሄደ ግንቦት 20 ፍጻሜውን እንደሚያገኝ ለማወቅ ተችሏል።