የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በመገምገም ላይ የሚገኙ ሲሆን በግምገማው አጀማመር ላይ ተገኝተው መድረኩን በንግግር የከፈቱት የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ገብሩ ባስተላለፉት መልዕክት በዩኒቨርሲቲያችን ከተለያዩ ኮሌጆች የቀረቡት የማኅበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ከት/ት ክፍል ጀምሮ የግምገማ ሂደት አልፈው የመጡ ከሃያ በላይ ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ገልጸው አሁን የሚደረገው ግምገማ ከዞኑ ከተለያዩ መምሪያዎች የተወከሉ ባለሙያዎችን ያሳተፈና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የሚደረግ መሆኑን አመላክተው በግምገማው ሂደት ለማኅበረሰቡ ሊጠቅሙ የሚችሉ ፕሮጀክቶች የሚመረጡበት እንደሚሆን ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል፡፡