farisውድ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች፣ተማሪዎች፣የአካባቢው ማህበረሰብ እና ሁሉም የባለድርሻ አካላት በሙሉ፡- የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሶስተኛው ፕሬዝዳንት ሆኜ ወደ ተቋሙ በመቀላቀሌ ላቅ ያለ ደስታ ይሰማኛል።
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሦስተኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲ ከመሆኑ አንጻር ጥሩ የመስራት አቅም ያላቸው ሰራተኞች፣ ሰላም ወዳድ የሆኑ ተማሪዎች እና የአከባቢው ማህበረሰብ መኖራቸው ለተቋሙ ምቹ የሆነ የስራ ከባቢን በመፍጠር ረገድ የጎላ ሚና ስላለው የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ዩኒቨርሲቲው በፍጥነት ለማደግ ምቹ የሆኑ እድሎች እንዲፈጠርለት አድርጎታል፡፡
ነገር ግን ከዚህ ምቹ የሆነ አጋጣሚ ጎን ለጎን እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ተግዳሮቶች እንዳሉም ይታመናል፡፡ ነገር ግን በየትኛውም አጋጣሚ የሚፈጠሩትን ተግዳሮቶችን በስራ ማሸነፍ የማይቀር ነው።
እኔ እንደምገነዘበው በዕድገት ጎዳና ላይ የሚገዳደረንን ተግዳሮትን ተሻግረን ካሰብነው ግብ መድረስ በዕድል የሚሆን አይደለም፡፡ በአንጻሩ ግን ይህንን ማሳካት የሚቻለው በቁርጠኝነት እና በቁርጠኝነት ብቻ ነው፡፡ የትናንሽ እንጨቶች ህብር (ጥምረት) የሚኖረው ጥንካሬ ከአንድ የእንጨት ጥንካሬ እንደሚበልጥ ሁሉ የመላው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና የሁሉም የባለድርሻ አካላት የጋራ ጥምረት የዩኒቨርሲቲውን ፈጣን እድገት በማረጋገጥ ረገድ የጎላ ሚና አላቸው። ስለሆነም ሁላችሁም እህቶች እና ወንድሞች በሙሉ ህልማችንን እውን ለማድረግ በጋራ እንድንተባበር ስል በትህትና እጠይቃለሁ።
ጥበብ የሁሉም ስኬት ዋና ቁልፍ ናት፡፡
ለጥበብ እንተጋለን!
ፋሪስ ዴሊል የሱፍ ( PhD)

Copyright © 2024. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT