በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በወልቂጤ ዩኒቪርሲቲ በአስ/ኮ/ማ/ም/ፕ/ጽ/ቤት በተማሪዎች ዲን ሥር በሚገኘው የስፖርትና መዝናኛ ቢሮ አማካይነት ተዘጋጅቶ ከመጋቢት 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ሲካሄድ የቆየው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ለውስጥ ስፖርታዊ ውድድር በዛሬው ዕለት ግንቦት 12/2015 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡
በዚህም መሠረት በሠራተኞች ዘርፍ የተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በጥምረት ከቀረቡት ኮምፒዊቲንግና እና ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ፣ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር ባደረጉት ውድድር የተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ቡድን በፍጹም ከጨዋታ ብልጫ ጋር 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫው አሸናፊ ሲሆን በተማሪዎች ዘርፍ የተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ከግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ኮሌጅ ጋር ባደረጉት ግጥሚያ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ኮሌጅ ቡድን 1ለ0 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል፡፡
ውድድሩም ፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት የተሞላበት፣ ወንድማማችነት የተንጸባረቀበት፣ደጋፊዎችን ቁጭ ብድግ ያሰኘ፣ማራኪ፣እና ደማቅ ነበር፡፡
በመጨረሻም ዶክተር የሻረግ አፈራ የአስ/ኮ/ም/ም/ፕ/ት እንዲሁም ካሳሁንአቤ (ረ/ፕ/ር) የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር እና የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትልፕሬዝዳንት ተወካይ ለአሸናፊዎች የዋንጫ ሽልማት እንዲሁም ለዳኞች፣ለኮከብ ግብ አስቆጣሪዎች እና ለልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች የምስክር ወረቀት አበርክተዋል።
ለጥበብ እንተጋለን !
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት