በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ጉዳይ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከ/መቆ/ዳይሬክቶሬት አመቻችነት በዓለም አቀፍ የትምህርት ተቋም አማካይነት ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለ100 ሴት ተማሪዎች የሚሰጠው የአመራርነት ስልጠና መሰጠት ጀመረ፡፡
ስልጠናው የሴቶችን አቅም በማጎልበት ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በሁለት ዙር ያከናወነውን የተሻለ የስልጠና አፈጻጸም መነሻ በማድረግ ሶስተኛው ዙር የስልጠናው ዕድል መሰጠቱን ስልጠናውን ካዘጋጁት አካላት ለማወቅ ተችሏል፡፡
ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ከወጣው የድርጊት መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለጥበብ እንተጋለን!
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት