አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ 2007 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 20 – 21 /2007 ዓ.ም ድረስ መሆኑን እየገለጽን ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ፡-

  1. የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤት ካርድ
  2. የ10ኛ ክፍል ማትሪክ ውጤት ካርድ
  3. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት ካርድ
  4. ከ 9ኛ - 12ኛ ክፍል የትራንስክሪፕት ውጤት
  5. 8 ጉርድ ፎቶግራፎች
  6. ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን የትምህርት ማስረጃዎች ኦሪጂናልና 2 የማይመለስ ኮፒ በመያዝ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እየገለጽን ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጸለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ዬኒቨርሲቲው ነባር ተማሪዎች ጥሪ ወደፊት የሚገለጽ ስለሆነ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራር ጽ/ቤት