በተማሪዎች ህብረት ስራ አስፈፃሚ (ዘርፎች) የሚከናወኑ ተግባራት
- አካዳሚክ ዘርፍ
- የየኮሌጁን አካዳሚክ ተጠሪዎች (የዲፓርትመንት እና ኮሌጅ ኮሚቴ)መከታተልና ተጠናክረው እንዲሰሩ ማድረግ፣
- በተማሪዎች መካከል ችግር ፈቺ የጥናታዊ ፅሁፎችና ፈጠራ ሥራዎች ውድድር ማካሄድ፣
- በትምህርት መርሀ ግብሩ በፈቃደኝነት አገልግሎት የሠጡ ተማሪዎችን በሥራቸው እውቅና እንዲያገኙ ማድረግ፣
- የመማር ማስተማሩ ሂደት በአግባቡ መካሄዱን ይከታተላል
- ተማሪዎች በት/ት ጉዳይ የሚገጥሟቸውን ችግሮች አብሮ ይፈታል
- የመረጃና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ
- አጠቃላይ የህብረቱን እንቅስቃሴ ለተማሪዎች በተለያዩ መንገዶች ማሳወቅ
- የተለያዩ ክበረ በአላት እና የተማሪዎች ባእላትን ያዘጋጃል
- ህብረቱን ከ ዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አካላት ጋር እና ከተማሪው ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንዲኖረው ማድረግ
- ልዩ የፓናል ውይይት ያዘጋጃል እንግዶችንም ይጋብዛል
- ህብረቱ ዓመታዊ መጽሔት እንዲኖረው ማድረግ፣
- የተለያዩ የኪነ ጥበባት መድረኮችን ማዘጋጀት፣
- የጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ
- አጠቃላይ የተማሪዎች አገልግሎቶቸን መከታተል እንደ አስፈላጊነቱ ሀሳቦችን መጠቆም
- የተማሪ መገልገያ ቁሳቁሶች እንደአስፈላጊነቱ እንዲጠገኑ ከሚመለከተው አካል ጋር መስራት፣
- ልብስ ንጽህና ሊሰጡ የሚችሉ አካላትን ማስገባት፣
- በየህንጻው ያሉ መጸዳጃ ቤቶችና መታጠቢያዎች ስራ እንዲጀምሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣
- የዲሲፕሊን ጉዳዮች ዘርፍ
- ተማሪውን በሚመለከቱ የዲስፕሊን ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ ይሆናል
- ተቀዋሙ የሚያወጣውን የተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ ለተማሪው ያሳውቃል
- በተለያዩ የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ከተማሪዎችና ከጠቅላላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር አብሮ መስራት፣
- ዲሲፕሊን ጥፋት ለሚፈፅሙ ተማሪዎች የተቋሙ ሰራተኞች በቂ መረጃ በማጠናቀር ከጥፋታቸው እንዲማሩ ማድረግና አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ፣
- የምግብ ዘርፍ
- ምግብ ሜኑ አቅርቦት ግዢ በተመለከቴ ከሚመለከተው ክፍል ጋር በመሆን በሂደቱ ይሳተፋል
- የምግብ ሜኑ በተማሪዎች ፍላጎት እና በጀት መጠን መሰራቱን ከሚመለከተው ጋር በመሆን ያረጋግጣል፤
- የሚቀርበው ምግብ፤ጥራት እቃዎች ንጽህና በአግባቡ መሆኑን በየቀኑ ያረጋግጣል
- ከምግብ ጋር ለሚፈጠሩ ችግሮች ከሚመለከተው ክፍል ጋር አፋጣኝ መፍትሄ ይፈልጋል
- ለተማሪዎች የተመደበ በጀት በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን አግባብነት ካለው አካል ጋር በመሆን ይቆጣጠራል፤
- .ስፖርትና መዝናኛ ዘርፍ
- በዲፓረትመንት እና በኮሌጆች ተማሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክሩ ስፖርታዊ ውድድሮቸን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ያዘጋጃል
- በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የተለያዩ የስፖርት እና የመዝናኛ ፌስቲቫሎቸ እንዲዘጋጁ ያደርጋል
- አስፈላጊ የሆኑ የስፖርት እና የመዝናኛ ቦታዎች ያመቻቻል
- ተማሪዎች የመዝናኛ አገልግሎት እንዲያገኙ አመቺ ሁኔታዎችን ይፈጥራል
- ተማሪዎች በተለያዩ ስፖርቶች እንዲሳተፉ ያበረታታል
- .የበጎ አድራጎት ዘርፍ
- በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች ተጨባጭ ሁኔታ አጥንቶ የሚደገፉበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡
- ተማሪዎች በቋሚነት ሊረዱ የሚችሉ አገልግሎቶችን ይሰጣል፣
- የሴቶች ጉዳይ ዘርፍ
- በህገ መንግስቱ የተደነገጉ የሴቶች መብቶች እንደተጠበቁ ሆኖ ሴት ተማሪዎች መሰረታዊ መብቶች መከበራቸውን ይከታተላል ያስከብራል
- ሴት ተማሪዎች የሚደርስባቸውን የአካል እና የስነ-ልቦና ጥቃት በማጥናት ይከላከላል፤ የምክር አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል
- ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጠየታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ልዩልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን በመለየት ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል
- በውጤታቸው ደከም ያሉ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲገኙ ማድረግ፣
- አዲስ ተመድበው ለሚመጡ ሴት ተማሪዎች አቀባበል ማድረግና በነባር ሴት ተማሪዎችና መምህራን ትምህርት ማሰጠት፣
- የአካል ጉዳተኞች ዘርፍ
- የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበራቸውን ያረጋግጣል
- በዶርሚተሪ፤ካፍቴሪያ፤በክሊኒክ፤በላይብረሪና በሌሎችም አገልግሎት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ልዩ ድጋፍ ማግኘታቸውን ያረጋግጣል
- አካል ጉዳተኞችን በማሰባሰብ ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፣
- በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እንዲሳተፉ ያደርጋል፣
- .የፋይናንስ ጉዳዮች ተጠሪ
- የህብረቱን ገቢና ወጪዎች ይቆጣጠራል
- የህብረቱን ሂሳብ በታወቀ የሂሳብ አሰራር መሰረት መንቀሳቀሱን ይቆጣጠራል
11.ክበባት እና ማህበራት
- የክበባት እና ማህበራትን መከታተል አዳዲስ ከበቦች እና ማህበራት እንዲኖሩ ድጋፍ ማድረግ
- ለክበባት እና ማህበራት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
- የተለያዩ በዩኒቨርሲቲው ብሎም በህብረቱ የሚሰጡትን በአላት በተሳካ ሁኔታ እንዲከበሩ ማድረግ
- የስነ-ጽሁፍ ምሽት ያዘጋጃል
- ለክበባት ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጅቶችን ያፈላልጋል