የ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በፕሮግራም በጀትና ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በውይይቱም ላይ በተለይም ሪፖርቱ 31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ በተካሄደበት ማግስት የቀረበ በመሆኑ በትምህርት ጉባዔው ላይ በትኩረት አቅጣጫነት የተነሱትን አንኳር ነጥቦችን መነሻ በማድረግ በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ጠቃሚ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ከተሰብሳቢዎች በተነሱት ጥያቄና አስተያየቶች ዙሪያ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና የየዘርፉ ሃላፊዎች ምላሽ ሰጥተውባቸዋል፡፡
ሪፖርቱ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እና በሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ መዘግየቱን የገለጹት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል ከማኔጅመንት ካውንስሉ አባላት ለተነሱት ጥያቄና አስተያየቶች የማጠቃለያ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡