"ፈጠራ ለአቪዬሽን ልህቀት!" በሚል መሪ-ቃል በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በሳይንስ ሙዚየም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ከትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ኤክስፖ ላይ ዩንቨርስቲያችን በመሳተፍ ላይ ይገኛል።
በSTEM ማእከላችን ስልጠና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ነቢሀ ነስሩ የአየር መንገዱን ስራ የሚያቀል የስልክ መተግበሪያ እንዲሁም ተማሪ በረከተአብ ምህረተአብ ለአቪዬሽን የሚያገለግል የራዳር ሲስተም በመስራት ኤክስፖው ላይ ለዕይታ አቅርበዋል፡፡
ኤክስፖው ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል እና የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሀንስ ገብሩ የተገኙ ሲሆን የቀረበውን የፈጠራ ስራዎች ተመልክተው ለተማሪዎቹ አድናቆታቸውን በመግለጽ እና በማበረታታት መልካም ውጤት እንዲገጥማቸውም ተመኝተዋል፡፡
በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተው የአቪዬሽን ኢኖቬሽን ኤክስፖ እስከ ታህሳስ 09/2016 ዓ.ም ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡