ላለፉት ሳምንታት ሰፊ ዝግጅቱን ሲያደርግ የቆየው ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው የምስረታ ታሪክ የመጀመሪያዎቹ የሆኑትን የበኩር የህክምና ዶክትሬት ተመራቂ ተማሪዎችን ዛሬ መስከረም 12/2015 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው በደማቅ ሁኔታ ለማስመረቅ እንዲህ ተዘጋጅቷል፡፡
የተከበራችሁ የዛሬው ተመራቂ ተማሪዎቻችን ያለፉትን ሰባት ዓመታት በተቋማችን ቆይታ አድርጋችሁ ፣የዕወውቀትን ገበያ ሸምታችሁ፣ሀገራችን ኢትዮጵያ በምትፈልጋችሁ ልክ በህክምናው ዘርፍ የዕውቀት ትጥቅን ታጥቃችሁ ፣የተለያዩ እንቅፋቶች ሳይበግራችሁ፣ ለዚህ ቀን ስለደረሳችሁ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡