የማኔጅመንት ካውንስል አባላት በዩኒቨርሲቲው የፕሮግራም በጀትና ዕቅድ ዳይሬክቶሬት የቀረበውን የተቋሙን የ2014ዓም የአፈጻጸም ሪፖርት ያደመጡ ሲሆን በቀረበውም የአፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ከተሰብሳቢዎች የተለያዩ ማብራሪያ የሚሹ ጥያቄዎችና ገንቢ የሆኑ አስተያየቶች ቀርበው በተነሱት ነጥቦች ዙሪያ የሚመለከታቸው ምክትል ፕሬዝዳንቶችና የስራ ክፍል ሃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውባቸዋል፡፡
በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል ማጠቃለያ የሰጡ ሲሆን በማጠቃለያቸው ላይም እንደገለጹት አጠቃላይ የተቋሙ አፈጻጸም ሲታይ በ2013 ዓ.ም ከነበረው 77.84% በ2014ዓ.ም አፈጻጸሙ ወደ
85.39% ከፍ ማለቱን ገልጸው በተቋም ደረጃ ለታየው እመርታ ዶክተር ፋሪስ ደሊል የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ በሙሉ አመስግነዋል፡፡ ዶክተር ፋሪስ አያይዘውም ሲገልጹ በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ከወዲሁ የአምስት ዓመቱ ስልታዊ እቅድ ክለሳ የተከናወነ መሆኑንና የ2015 ዓም ዕቅድ ተዘጋጅቶ የተጠናቀቀ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ በጀትን በአግባቡና በውጤታማነት ለመጠቀም፣ ከ2015 ዓም ጀምሮ ለተማሪዎቻችን የመውጫ ፈተና (EXIT EXAM) የሚዘጋጅ ስለሆነ በዚህ ሂደት ውጤታማ የሆነ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ባለድርሻ አካላት ተግተው እንዲሰሩ ካሳሰቡ በኋላ የማኔጅመንት ካውንስል አባላቱ ስብሰባ ተጠናቅቋል ፡፡