ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በቴማቲክ ሪሰርች "Thematic Research" ዝግጅት ዙሪያ ለመምህራኖቹ የግንዛቤ ማስጨቀጫ መድረክ አካሔዷል
የግንዛቤ መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት በዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ዮሀንስ ገብሩ እንደገለፁት ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ዘርፎች ምርምሮች በስፋት ሲሰሩ እንደነበር በመጥቀስ ዛሬ የተዘጋጀው የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክም በዘንድሮው አመት ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የሚሰሩ ምርምሮች "Thematic" እንዲሆኑ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት አቅጣጫውን ተከትሎ ለመስራት እንዲቻል ለመምህራኑ ግንዛቤ ለመፍጠር እና ለመመካከር በማሰብ ነው ብለዋል።
በእለቱም በዩኒቨርሲቲው የምርምር ዳይሬክተር በሆኑት በዶክተር ተሾመ ይትባረክ አማካይነት የ"Thematic Research" ፅንሰ ሃሳብ የያዘ ፅሁፍ በዝርዝር ቀርቧል።
በመጨረሻም እንዴት አድርገን እንስራው በሚሉ ሃሳቦች ላይ የውይይቱ ተሳታፊ በሆኑት የዩኒቨርሲቲው መምህራን ሀሳብ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎችም በም/ማ/አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ገብሩ እና የምርምር ዳይሬክተር በሆኑት ዶ/ር ተሾመ ይትባረክ ምላሽ ተሰጥቷል።
ለጥበብ እንተጋለን!
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት