የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀውና በጉራጌ ዞን ስር በሚገኙ የመንግስት ሆስፒታሎች በነርሲንግ ሙያ ላይ ተሰማርተው ለሚያገለግሉ ባለሙያዎች “Improving Nursing Care Service through Timely ,Purposive and Integrated Nursing Round ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ስልጠና ተሰጠ፡፡
በስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት ቸርነት ዘርጋ (ረ/ፕ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት ዩኒቨርሲቲው ለመስራት ካቀዳቸው ስራዎች መካከል አንዱ ለጤናው ዘርፍ ትኩረት በመስጠት ጤናማ የሆነ ማህበረሰብን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት እንደተቋም ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን በመወጣት ረገድ የጤና ባለሙያዎችን ብቃት የሚያሻሽሉ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ብቁ የሆነ ባለሙያ ለማፍራት በትጋት መስራት መሆኑን በመግለጽ ሰልጣኞች ከስልጠናው በቂ የሆነ ግብዓት እንደሚያገኙ ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው በነርሲንግ የትምህርት ክፍል መምህራን አማካይነት የሚሰጥ ሲሆን የስልጠናውም ዓላማ የተቀናጀ ህሙማንን የመጎብኘት (Nursing Round) ስርዓትን በጉራጌ ዞን ስር በሚገኙ ሆስፒታሎች በስፋት ማስጀመር፣ የነርሲንግ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማሻሻል እና የታካሚዎች የአገልግሎት እርካታን መጨመር ሲሆን ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከነርሲንግ የትምህርት ክፍል ጋር በጋራ ቅንጅት በመፍጠር ስልጠናው መዘጋጀቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለጥበብእንተጋለን!
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት