ዩኒቨርሲቲያችን በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት የተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ( University of Applied Sciences) መካከል አንዱ ሲሆን በተለይም የተሻለ አቅም እና ልምድ ካላቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በተለይም በተማሪዎች ልውውጥ ( Students Exchange) ላይ መሰረት አድርጎ የመግባቢያ ሰነዶችን በመፈራረም እና ወደ ተግባር በመግባት ረገድ በትኩረት መስራት ይጠበቅበታል፡፡
ይህንን መሰረት በማድረግ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተሻለ ልምድ ለመቅሰም ይረዳው ዘንድ በጀመረው ስራ መሰረት ስዊዘርላንድ ሀገር ውስጥ ከሚገኘው Lucerne University of Applied Sciences ጋር የተማሪዎች ልውውጥ ( Students Exchange) ለማድረግ በፈጠረው ስምምነት መሰረት "Advanced solar training" የሚባል ኮርስ ለመውሰድ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን የመጡትን 15 ተማሪዎችን በመቀበል ለ10 ተከታታይ ቀናት በቆየ ስልጠና ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ ስልጠናው የተጠናቀቀ ሲሆን በስልጠናውም ላይ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ 14 ተማሪዎችና 3 መምህራን እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡