ሐምሌ 10 2015 ዓ.ም በአንድ ቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተላለፈውን ሀገራዊ ጥሪ ዕውን ለማድረግ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ባሳተፈ መልኩ ከ5000 በላይ ችግኞችን በመትከል እንደሀገር የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ለመወጣት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አዘጋጅቷል፡፡
ስለሆነም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ በነገው ዕለት ጠዋት 3፡00 ላይ በትምህርትና ስነባሕሪ ሳይንስ ኮሌጅ ፊት ለፊት በሚገኘው የሰራተኞች ካፍቴሪያ በመሰባሰብ በችግኝ ተከላው ላይ በመሳተፍ አረንጓዴ አሻራችሁን እንድታኖሩ በማለት ዩኒቨርሲቲው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ለጥበብ እንተጋለን!
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት