ክፍት የሥራ ቦታ

ማስታወቂያ

ለድህረ -ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በድህረ ምርቃ ፕሮግራም በመደበኛውና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ባሉት ፕሮግራሞች አመልካቾችን አወዳድሮ ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

Read more ...

ለነባር የክረምት ትምህርት ተማሪዎች በሙሉ

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በክረምት መርሀ-ግብር ትምህርታችሁን ለምትከታተሉ ነባር

Read more ...

“ጉዞ ወደ አረንጓዴ ልማት” በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ልማትና ባህል ማዕከል አማካይነት የተዘጋጀው 11ኛው ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት በጉራጌ ዞን በአበሸጌ ወረዳ ጀጀባና ጋሶሬ ቀበሌ ከፌዴራል ፣ ከክልል፣ ከጉራጌ ዞን፣ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ከሁሉም የዞኑ ወረዳዎች የተዉጣጡ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚኖሩ የብሔረሰቡ ተወላጆች እንዲሁም የቀበሌዉ ነዋሪዎች በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ርስቱ ይርዳው ባስተላለፉት መልዕክት ለ11 ተከታታይ አመታት ሳይቋረጥና ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ በተደራጀና በደመቀ ሁኔታ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙትን የዞኑ ተወላጆች እና የሌሎች አካባቢ ተወላጆች እያሰባሰበ በመከናወን ላይ ያለው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ውጤታማነቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል የግብርና ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ክቡር አቶ ኡስማን ስሩር በበኩላቸዉ ባስተላለፉት መልዕክት ግብርና የሀገራችን ትልቁ የዕድገት መሠረት መሆኑን ገልጸው የተፋጠነ ዕድገት ለማስመዝገብ ግብርናችንን ማዘመን እንደሚገባ እና ይህንንም እውን ለማድረግ የተፈጥሮ ሀብት ልማታችንን በአግባቡ በመያዝ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብራችንን በስፋት አጠናክረን መቀጠል እንደሚገባን አብራርተዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአየር ንብረት መዛባት ከፍተኛ ዋጋ ከሚያስከፍላቸው ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን አስታውሰው የተፈጥሮ ሀብት አያያዛችንንና አጠቃቀማችን በማሻሻል ፣ የተራቆቱ አካባቢዎችን መልሶ በማልማት የአካባቢው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ከፍ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ በበኩላቸዉ ማህበሩ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ሁለት እሴቶችን መሰረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጸው የመላዉ ህዝብ የጋራ ፍላጎት ተብለዉ በተለዩ የልማት ስራዎች ለአብነት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ ጅምር ስራዎች ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ማዕከል ግንባታ ፣የቡታጅራ ከተማ የዋና ጽህፈት ቤትና ቢዝነስ ማዕከል፣ በትምህርት በጤና በኑሮ ማሻሻል ፕሮግራምና በሌሎችም ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ ልማቶች በጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር አማካይነት እየተከናወነ እንደሆነም አብራርተዋል።

የችግኝ ተከላው መርሀ ግብር እንዲሳካ በማድረግ ረገድ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ላደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍና ዩኒቨርሲቲው ላበረከተው ትልቅ አስተዋጽኦ ከጉራጌ ልማትና ባህል ማዕከል የተዘጋጀውን የምስጋና እና የዕውቅና የምስክር ወረቀት ክቡር ዶክተር ፋሪስ ደሊል የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ከሆኑት ከክቡር አቶ ርስቱ ይርዳው እጅ ተቀብለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪም የፊታችን ሐምሌ 10 2015 ዓ.ም በአንድ ቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተላለፈውን ሀገራዊ ጥሪ ዕውን ለማድረግ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ያሳተፈ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ለማከናወን ሰፊ የሆነ ዝግጅት አድርጓል።

ከዚህም ባሻገር ዘንድሮ ለ3ኛ ዙር የሚካሄደውና 15 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የኬሮድ ታላቁ የጎዳና ላይ ሩጫ “ለሰላማችን እንሮጣለን“ በሚል መሪ ቃል መነሻውን ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መድረሻውን ወልቂጤ ከተማ በማድረግ በነገው ዕለት ይከናወናል፡፡

ለጥበብ እንተጋለን!

We Strive for Wisdom!

Wolkite University Public & International Relation Directorate

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በመገምገም ላይ ይገኛሉ

Read more ...

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የጨቅላ ሕጻናት የእንክብካቤ ማዕከል እና የመምህራን መኖሪያ በሆነው አፓርታማ ግቢ ውስጥ የሚገኘው ሞዴል የማህበረሰብ መድሃኒት ቤት በይፋ ተመረቁ

Read more ...

በ2014 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ለመተግበር በዋቤ ችግኝ ጣቢያ የተዘጋጁት ችግኞችን አስመልክቶ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የስፔሻሊቲ የትምህርት ፕሮግራሞችን መስጠት ጀመረ

Read more ...

We have 206 guests and no members online

Wolkite University, P.O.Box 07, Wolkite, Guragie Zone, SNNPR, Ethiopia | +251-113-220042 | pird@wku.edu.et/president@wku.edu.et

Copyright © 2023. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT