ክፍት የሥራ ቦታ

ማስታወቂያ

ለድህረ -ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በድህረ ምርቃ ፕሮግራም በመደበኛውና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ባሉት ፕሮግራሞች አመልካቾችን አወዳድሮ ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

Read more ...

ለነባር የክረምት ትምህርት ተማሪዎች በሙሉ

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በክረምት መርሀ-ግብር ትምህርታችሁን ለምትከታተሉ ነባር

Read more ...

የምስጋና በጎ አድራጎት ድርጅት፣ጋአት ፋውንዴሽን፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና የጉራጌ ዞን ትምህርት ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በጉራጌ ዞን ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማ/ኮሌጆች፣ ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂን እና ሰው ሰራሽ አስተውሎ (Artificial Intelligence) ለመተግበር የሚያግዙ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረጉ

የምስጋና በጎ አድራጎት ድርጅት፣ጋአት ፋውንዴሽን ፣የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና የጉራጌ ዞን ትምህርት ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በጉራጌ ዞን ለሚገኙ 4 የኮንስትራክሽን እና ኢንደስትርያል ኮሌጆች፣ ለ10 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ለ10 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂን እና ሰው ሰራሽ አስተውሎ (Artificial Intelligence) ለመተግበር የሚያግዙ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረጉ ፡፡

በድጋፍ አሰጣጡ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ እና የምስጋና በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች የሆኑት ክቡር አምባሳደር ምስጋናው አርጋው ባስተላለፉት መልዕክት በህይወት ዘመናችን ያገኘነው ትልቅ ሀብት ትምህርት መሆኑን ፣ለትምህርት የምናጠፋው ጊዜ ተገቢ መሆኑን፣ለብዙ ጥፋቶቻችን መነሻው ትምህርት አለማግኘታችን መሆኑን ፣ በሰዎች መካከል ያለው ልዩነት አንዱ ጉዳይ በመማር እና ባለመማር መካከል ያለው ልዩነት መሆኑን፣ በበለጸጉትና ባልበለጸጉት ሀገራት መካከል ያለው ልዩነት በሳይንስ ፣ቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራዎች ጠንካራና ደካማ የመሆን እና ያለመሆን ልዩነት መሆኑን ፣ በትምህርት አማካይነት የችግር አፈታት አቅማችን ካደገ የትም መኖር እንደምንችል፣ በትምህርት ጥራት ላይ ስነሰራ አጠቃላይ የትምህርት ስነምህዳሩን ማሻሻል ብቻ ሳይሆን የማህበረሰብ ለውጥ ላይ ጭምር መስራት እንደሚገባን ገልጸው የምስጋና በጎ አድራጎት ድርጅትም ይህንን መሰረት በማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን በመግለጽ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በመሰል ተግባራት ላይ በመሳተፍ የሚጠበቅበትን ግዴታ ሊወጣ እንደሚገባ አጽንኦት በመስጠት አሳስበዋል፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል በበኩላቸው የምስጋና በጎ አድራጎት ድርጅትን እና ጋአት ፋውንዴሽንን አመስግነው የትምህርት ጥራትን ማሻሻል የህልውና ጉዳይ መሆኑን በመግለጽ እንደዚህ ዓይነት ድጋፎች በፈጠራው ስራ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸውን ታዳጊዎች በእጅጉ ስለሚያበረታቱ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ ሆኖም በሀገራችን ላለፉት በርካታ አመታት የተከተልነው የትምህርት ስርዓት እና የተገበረንብት መንገድ እጅግ የተሳካ እንዳልነበር አስታውሰው በ2014 የተመዘገበው 12ኛ ክፍል የሀገር-አቀፍ ፈተና የውጤት መዝቀጥ ጥሩ ማሳያ መሆኑና ገልጸዋል፡፡

ዶክተር ፋሪስ አያይዘው ይህ የትምህርት ዘርፍ ስብራት ለመጠገን በርካታ የሪፎም ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ለውጤታማነቱ ግን በመንግስት ብቻ ሳይሆን የብዙሀን ባለ ድርሻ አካላት ርብርብ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

ዶክተር ፋሪስ አያይዘውም ከዞኑ ሁሉም አካባቢዎች የተውጣጡ የአጠቃላይ ትምህርት ተማሪዎች በክረምት የፈጠራ ችሎታቸውን በSTEM (Science, Technology, Engineering and Mathematics) ቤተ- ሙከራዎች እያጎለብቱ መቆየታቸውን ገልጸው ከ2013 ጀምሮ STEM POWER የራሱን ማዕከል ከፍቶ የተለያዩ ተማሪዎችን በማዕከሉ በመቀበል የፈጠራ ልምምድ እንዲያደርጉ ብቻ ሳይሆን ተስፋ ሰጪ ጅምሮችም እየታዩበት መሆኑን አስታውሰው ለብዙ ወጣቶች አርዓያ የሆነውና የብዙ ፈጠራዎች ባለቤት ተማሪ ኢዘዲን ካሚልም የዚህ STEM POWER ፍሬ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የጋአት ፋውንዴሽን ተወካይ ባስተላለፉት መልዕክት የጋአት ፋውንዴሽን በአሜሪካን ሀገር በሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሆኑ የጉራጌ ተወላጆች አማካይነት የተቋቋመ ፋውንዴሽን መሆኑን ገልጸው የተመሰረተበት ዓላማ 1ኛ. የትምህርት ቤቶችን የማስፈጸም አቅም ለመገንባት 2ኛ. መምህራንን ለማሰልጠን 3ኛ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የስኮላርሺፕ ዕድል ለመስጠት 4ኛ ኮዲንግን የአፍ መፍቻ ቋንቋ አድርጎ ለመጠቀም መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አስከብር ወልዴ ባስተላለፉት መልዕክት የምስጋና በጎ አድራጎት ድርጅት፣ጋአት ፋውንዴሽን እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን አመስግነው በተለይም የምስጋና ፋውንዴሽን በጉራጌ ዞን ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን በማስገንባት ትልቅ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸው በዞኑ ደረጃ አስፈላጊው የትምህርት ፋሲሊቲ ወይም ግብአቶች በበቂ መልኩ ተሟልቶላቸው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት ትምህርት ቤቶች 43% ብቻ በመሆናቸው ቀሪዎቹን የግብአት ችግር ያለባቸውን ለማጠናከር የምስጋና በጎ አድራጎት ድርጅት፣ጋአት ፋውንዴሽን እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በመሆን በጉራጌ ዞን ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማ/ኮሌጆች፣ ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂን እና ሰው ሰራሽ አስተውሎ (Artificial Intelligence) ለመተግበር የሚያግዙ ቁሳቁሶችን መለገሳቸው እጅግ የሚበረታታና ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም በጉራጌ ዞን ለሚገኙ 4 የኮንስትራክሽን እና ኢንደስትርያል ኮሌጆች፣ ለ10 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ለ10 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂን እና ሰው ሰራሽ አስተውሎ (Artificial Intelligence) ለመተግበር የሚያግዙ ቁሳቁሶች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የምስጋና በጎ አድራጎት ድርጅት፣ጋአት ፋውንዴሽን ፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና የጉራጌ ዞን ትምህርት ጽ/ቤት በቀጣይ በጋራ አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ከመፈራረማቸው ባሻገር በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ የዕለቱ የክብር እንግዳና የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች የSTEM ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በመገምገም ላይ ይገኛሉ

Read more ...

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የጨቅላ ሕጻናት የእንክብካቤ ማዕከል እና የመምህራን መኖሪያ በሆነው አፓርታማ ግቢ ውስጥ የሚገኘው ሞዴል የማህበረሰብ መድሃኒት ቤት በይፋ ተመረቁ

Read more ...

በ2014 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ለመተግበር በዋቤ ችግኝ ጣቢያ የተዘጋጁት ችግኞችን አስመልክቶ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የስፔሻሊቲ የትምህርት ፕሮግራሞችን መስጠት ጀመረ

Read more ...

We have 326 guests and no members online

Wolkite University, P.O.Box 07, Wolkite, Guragie Zone, SNNPR, Ethiopia | +251-113-220042 | pird@wku.edu.et/president@wku.edu.et

Copyright © 2023. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT