ክፍት የሥራ ቦታ

ማስታወቂያ

ለድህረ -ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በድህረ ምርቃ ፕሮግራም በመደበኛውና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ባሉት ፕሮግራሞች አመልካቾችን አወዳድሮ ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

Read more ...

ለነባር የክረምት ትምህርት ተማሪዎች በሙሉ

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በክረምት መርሀ-ግብር ትምህርታችሁን ለምትከታተሉ ነባር

Read more ...

 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሁለት መቶ ለሚሆኑ ተመራቂ ሴት ተማሪዎች ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የፕሬዝዳንሻል ሜንተርሽፕ ስልጠና መስጠት ጀመረ

ስልጠናውን ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ጉዳዬች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀብቴ ዱላ ተማሪዎች እስካሁን በግቢው ውስጥ የነበራቸው ቆይታ ስኬታማ በመሆኑ ለመጨረሻዋ የትምህርት መንፈቅ አመት ደርሰዋል በማለት አሁንም ከፊት የሚጠብቃቸውን የመውጫ ፈተና ለማለፍ በተለመደው ብርታታቸው በትጋት እንዲዘጋጁ አሳስበዋል፡፡
የመማር ማስተማር ጉዳዬች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ካሳሁን አቤ በስልጠና ማስጀመሪያ መድረኩ የተገኙ ሲሆን ሴትነት በራሱ መሪነት ነው በማለት ዛሬ ጀምሮ የሚሰጠው ስልጠናም ሴት ተማሪዎች ብቁ መሪ በመሆን ከራሳቸው አልፈው ሀገር ለመምራት የሚያስችል አቅም የሚሰጥ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡ ረ/ፕ ካሳሁን አያይዘውም ነገ ብቁና ተመራጭ መሪ ለመሆን የዛሬው የትምህርት ብቃት ዋናው መሰረት ነው በማለት ቀሪውን ጊዜ በአግባቡ ለመውጫ ፈተና ዝግጅት በመጠቀም ሀላፈነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
የዩኒቨርስቲው የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ኤችአይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት አስራት እንደገለፁት ይህ ስልጠና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከአለም አቀፍ የትምህርት ተቋም /Institute of International Education/ ከተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው:: የስልጠናው ተሳታፊ ሴት ተማሪዎች በያዝነው አመት የሚመረቁ ሲሆኑ ስልጠናውም የአመራር ሰጪነት ክህሎታቸውን በማዳበር በየስራ ዘርፉ ሲሰማሩ ብቁ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ እንደሆነ ዳይሬክተሯ አያይዘው ገልፀዋል፡፡
ስልጠናውን የሚሰጡት የዩኒቨርሲቲው መምህር የሆኑት መምህርት ይገረሙ ክፍሌ እና መምህርት ፌቨን ዬሀንስ ሲሆን "Entrepreneurship, career development and presentation skill" በሚሉ ርዕሶች ላይ የሚያተኩር ነው፡፡

የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በመገምገም ላይ ይገኛሉ

Read more ...

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የጨቅላ ሕጻናት የእንክብካቤ ማዕከል እና የመምህራን መኖሪያ በሆነው አፓርታማ ግቢ ውስጥ የሚገኘው ሞዴል የማህበረሰብ መድሃኒት ቤት በይፋ ተመረቁ

Read more ...

በ2014 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ለመተግበር በዋቤ ችግኝ ጣቢያ የተዘጋጁት ችግኞችን አስመልክቶ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የስፔሻሊቲ የትምህርት ፕሮግራሞችን መስጠት ጀመረ

Read more ...

We have 252 guests and no members online

Wolkite University, P.O.Box 07, Wolkite, Guragie Zone, SNNPR, Ethiopia | +251-113-220042 | pird@wku.edu.et/president@wku.edu.et

Copyright © 2023. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT