የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ በፕሮግራም በጀትና ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው የሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡባቸው ሲሆን የማጠቃለያ ሃሳብ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በዶክተር ፋሪስ ደሊል አማካይነት ለዩኒቨርሲቲው የካውንስል አባላት ቀርቧል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የ2015 ዓ.ም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ፕሮጄክት ጽ/ቤት የ3ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ የሆነ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የካውንስል አባላት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ካዳመጡ በኋላ በመገንባት ላይ ያለውን የዩኒቨርሲቲውን የአስተዳደር ህንጻ እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዋቤ የንግድና ማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝን ጎብኝተዋል፡፡
በቅድሚያ የተጎበኘው ባለ አምስት ወለሉ በ8000 ካሬ ላይ ያረፈው የአስተዳደር ህንጻ ሲሆን ይህ ህንጻ ስምንት ብሎኮች ያሉት ሆኖ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከ300 በላይ ክፍሎችን የያዘ፣ አንፊ ቲያትር ያለው፣ በአንድ ጊዜ እስከ 17 የሚደርሱ መኪናዎችን ፓርክ ማድረግ የሚችል፣ 400 መቀመጫ ያለው አዳራሽ ያለው፣ ለእያንዳንዱ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና ዳይሬክተሮች የሚያገለግሉ 13 ሚኒ አዳራሾች ያሉት፣ ከመሬት በላይ ክሎክ ታወሩን ጨምሮ 33 ሜትር ከፍታ ያለው መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት በባለሙያዎች አማካይነት ገለጻ ተደርጓል፡፡
በመቀጠልም የዋቤ የንግድና ማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝን አስመልክቶ በኢንተርፕራይዙ ስራ አስኪያጅ በሆኑት በአቶ አዲሱ እጥፉ አማካይነት ሰፊየሆነ ገለጻ የተደረገ ሲሆን በከብቶች መኖ ማቀነባበር፣ በፍየል እና ከብት ማደለብ፣ በወተት ከብት እርባታ እና በልዩ ልዩ ሰብሎች የማምረት ስራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኘው ይህ ኢንተርፕራይዝ እጅግ አበረታች በሆነ ጅምር ስራ ላይ እነደሚገኝ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የካውንስል አባላት በጉብኝቱ ወቅት በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡
ለጥበብእንተጋለን!
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት