ከታህሳስ 21/2015 ዓ.ም ጀምሮ “በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና “ በሚል ርዕስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየውና የዪኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ፣መምህራንና የቴክኒካል ረዳቶች የተሳተፉበት የምሁራን የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ::
የዪኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ፣መምህራንና የቴክኒካል ረዳቶች ለውይይት መነሻ በቀረበው ጽሁፍ ላይ ሰፊ የሆነ ውይይት በማድረግ እና የተለያዩ ምላሽና ማብራሪያ የሚሹ ጠቃሚ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን በተነሱት ጉዳዮች ዙሪያ የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በሆኑት በክቡር ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በዶክተር ፋሪስ ደሊል የማጠቃለያ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን በማጠቃለያ መድረኩ ላይ እንደተገለጸው ለሀገር ዕድገት የምሁራን ሚና የማይተካ መሆኑን፣ ያለምሁራን ድጋፍና ተሳትፎ የትም መድረስ እንደማይቻል፣ከውይይቱ የተገኙት ግብዓቶች በቀጣይ ሀገረ - መንግስት ግንባታው ላይ ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው፣ በውይይት መድረኩ የተነሱትን ነጥቦች በመውሰድ የሀገሪቱ የዕቅድ አካል ለማድረግ መንግስት ቁርጠኛ የሆነ አቋም እንዳለው እና ምሁርም ሆነ ፖለቲከኛ ከሀገሪቱ የፖለቲካ ስርዓት ውጭ ስላልሆኑ በጋራ በመቆም በሀገር ግንባታው ላይ ሰፊ የሆነ ድርሻችንን ልንወጣ እንደሚገባ በማጠቃለያው ላይ በስፋት ተገልጿል፡፡
“ለጥበብ እንተጋለን!”
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት