የእንሰት ምርት ማቀነባበሪያ ማሽን ለተጠቃሚዎች የማከፋፈል ሥራ ቀጥሏል
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2016/2017ዓ.ም በGIZ Ethiopia የገንዘብ ድጋፍ "Comprehensive Understanding of the Enset Processing Machine: Benefits to the Local Community and Its Influence on Food Securit” በሚል ርዕስ በተነደፈው ፕሮጀክት አማካይነት የተዘጋጀው እና ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ሲደረግ የቆየው የእንሰት ምርት ማቀነባበሪያ ማሽን በዛሬው ዕለት በእዣ ወረዳ ዴሰነ ቀበሌ ለተደራጁ ወጣቶች ርክክብ የተደረገ ሲሆን በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሀንስ ገብሩ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡