ማስታወቂያ

National Exit Model Examination Schedule

National Exit Model Examination Schedule of Examinees assigned in Wolkite University. Students who need account activation can go to Central Library starting from tomorrow  morning

Read more ...

ማስታወቂያ

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባቹህ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፣

Read more ...

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ማለፋችሁን ያረጋገጣችሁ

Read more ...

 

ስልጠናው ከመቀሌ፣አክሱም፣አዲግራት፣እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በጊዜያዊነት ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለመጡት ተማሪዎች የተዘጋጀ ሲሆን በፀጥታ ችግሮች ምክንያት የሥነ-ልቦና ጉዳት የደረሰባቸውን ተማሪዎች ለመርዳት ታስቦ በMental Health, Stress Management, Post-traumatic stress disorder, Grief Management, Resilience, Emotional Regulation, Anger Management, Helping behavior’s በሚሉት ርዕሶች ዙሪያ ስልጠናው የተዘጋጀ መሆኑን የስልጠናው አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡ ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ረ/ፕሮፌሰር ካሳሁን አቤ ሲሆኑ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንደገለጹት ስልጠናው የትህነግ ወራሪ ኃይል በከፈተው ጦርነት ሳቢያ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ተመድበው የመጡ ተማሪዎቻችን የስነልቡና ችግርና ማህበራዊ ቀውስ እንዳይገጥማቸውና በትምህርታቸው ላይ አሉታዊ የሆነ ተጽዕኖ እንዳያሳድርባቸው በማሰብ ይህ ስልጠና መዘጋጀቱን ገልጸው ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ሊያጋጥማቸው የሚችል ማናቸውም ዓይነት ችግር ካለ ተቋሙ ተገቢውን አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንና ከጎናቸው መሆኑን ጭምር አረጋግጠዋል።

ለችግሩ ለተዳረጉት ተማሪዎች የሥነ-ልቦና ድጋፍ ለማድረግ በተዘጋጀው በዚሁ ስልጠና ላይ ስልጠናውን ለመስጠት ከሳይኮሎጂ የትምህርት ክፍል የተውጣጡ ምሁራን ተሳትፈውበታል።

በስልጠናው ላይ ከተካፈሉት ተማሪዎች መካከል አስተያየታቸውን የሰጡን እንደገለጹልን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ምኞትና ፍላጎት ሰላሟ የተጠበቀና በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን ማየት ሆኖ እያለ አፍራሽ ድርጊቶችን በሚፈፅሙት ግለሰቦችና ቡድኖች እኩይ ሀሳብና ተልዕኮ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የስነልቡና ጫና መድረሱን አስታውሰው የዚህም ችግር ሰለባ ከሚሆኑት የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ ተማሪዎች በግንባር ቀደም የሚጠቀሱ በመሆናቸው በዚህም ምክንያት የስነ- ልቡና ጉዳት የደረሰባቸውን ተማሪዎች ለመደገፍ ታስቦ ስልጠናው በመዘጋጀቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ስልጠናውን ያዘጋጀውን አካል አመስግነዋል፡፡

በተጨማሪም በሥነ-ልቦና፣ በማህበራዊ ኑሮ፣ በባሕል፣ በወግ፣ ልማድና በልዩ ልዩ ማህበራዊ መስተጋብሮች የጠነከረ፣ የተሳሰረና የጠበቀ አንድነት እንዲኖረን ስልጠናው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ሲሉ የስልጠናው ተሳታፊ ተማሪዎች ገልጸዋል ፡፡

ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት (ከታህሳስ 13-14/2014 ዓም) የሚሰጥ ሲሆን 500 ተማሪዎች በስልጠናው ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡