ማስታወቂያ

National Exit Model Examination Schedule

National Exit Model Examination Schedule of Examinees assigned in Wolkite University. Students who need account activation can go to Central Library starting from tomorrow  morning

Read more ...

ማስታወቂያ

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባቹህ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፣

Read more ...

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ማለፋችሁን ያረጋገጣችሁ

Read more ...

 

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከሚገኙት ኮሌጆች መካከል አንዱ የሆነው የትምህርትና ስነ-ባህሪ ኮሌጅ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን በማስፋፋት፤ የተቋሙን የትምህርት ተደራሽነት ከፍ ከማድረግ አንጻር አዳዲስ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን ለመክፈት ተገቢውን የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማድረግ፤ ከሰው ሀይልና ከቁሳቁስ ጋር በተገናኘ ያለውን የቅድመ ዝግጅት ሁኔታ በማረጋገጥ፤ በቀጣይ ለመክፈት በዕቅድ በተያዙት አራት የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ላይ በዛሬው ዕለት የስርዓተ ትምህርት ግምገማ ወርክሾፕ አካሄደ:: በቀጣይ እንዲከፈቱ ለውይይት የቀረቡት አዳዲስ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች :-

  1. MA in counselling psychology
  2. MA in special Needs Education
  3. MA in Educational Leadership
  4. MA in Curriculum and Instruction መሆናቸውን ፕሮግራሙን ያዘጋጀው ክፍል ገልጿል:: ወርክሾፑን በንግግር የከፈቱት የትምህርትና ስነባህሪ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ጌቱ ደጉ ሲሆኑ እሳቸውም በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንደገለጹት ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እንደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋምነቱ ከተሰጡት ተልእኮዎች መካከል አንዱ የመማር ማስተማር ስራ መሆኑን አስታውሰው በዚህ ረገድ ተፈላጊ ፕሮግራሞችን በዓይነትና በብዛት በመክፈት፤ በተለይም የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን በማስፋፋት፤ የተቋሙን ተደራሽነት ማረጋገጥ ከዩኒቨርሲቲው የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን አብራርተው ዛሬ በዚህ ወርክሾፕ ላይ የቀረቡት የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሂደታዊ ጉዞአቸውን ጠብቀው እዚህ እንዲደርሱ ያልተቆጠበ ሙያዊ እገዛቸውን ላበረከቱትና ከፍተኛ የሆነ ጥረት ላደረጉት የዘርፉ ባለሙያዎች ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል::

በወርክሾፑ ላይ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት ዲን የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ቸርነት ዘርጋ እና የተቋማዊ ጥ/ማ/ማ/ዳይ/ዳይሬክተር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ብዙአለም አሰፋ የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተጋበዙ የትምህርት ባለሙያዎች በወርክሾፑ ላይ ተገኝተው በቀረቡት አዳዲስ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ላይ ገንቢ የሆኑ የማሻሻያ ሀሳቦችን አቅርበውና የቀረቡት ጠቃሚ ሃሳቦችም እንዲካተቱ ተደርገው ወርክሾፑ ተጠናቅቋል::