ማስታወቂያ

National Exit Model Examination Schedule

National Exit Model Examination Schedule of Examinees assigned in Wolkite University. Students who need account activation can go to Central Library starting from tomorrow  morning

Read more ...

ማስታወቂያ

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባቹህ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፣

Read more ...

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ማለፋችሁን ያረጋገጣችሁ

Read more ...

 

በትምህርት ሚኒስቴር የሂሳብና ሳይንስ ትምህርቶች ማሻሻያ ማዕከል ከዩኔስኮ ፤ ስቴም ሲነርጂ ፤ ስቴም ፓወር ፤ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ሚኒመም ለርኒንግ ኮምፒተንሲ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የዓለም ዓቀፍ የሳይንስ ቀንን በሀገር አቀፍ ደረጃ ከህዳር 20-24/2014 ዓም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አማካይነት በሳይንስ አውደ ርዕይ ያከበረ ሲሆን በአውደ ርዕይ ላይ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የስቴም ማዕከል ላደረገው ተሳትፎ ከሳይንስ ፈጠራ ስራ ሀገር አቀፍ ውድድር የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል::

ከዚህም በተጨማሪ በስቴም ማዕከላት መካከል በኢንጂነርንግ ዘርፍ ለ6ኛ ጊዜ በተካሄደው የሳይንስ ውድድር ላይ ተሳትፎ ባስመዘገበው የላቀ ውጤት ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን በመወከል የተሳተፈው ይድነቃቸው ተክሉ ወልደሰንበት በሳይንስ ፈጠራ ስራ በኢንጂነሪንግ ዘርፍ የ3ኛ ደረጃን አግኝቷል :: በተገኘው ውጤት እጅግ ደስ ብሎናል እንኳን ደስ ያላችሁ!

ይህ ውጤት ዩኒቨርሲቲያችንን ይበልጥ ሊያጠናክርና በቀጣይ ለተሻለ ውጤት እንድንሰራ የሚያበረታታንና የሞራል ስንቅ የሚሆነን ሲሆን በተለይ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል በዚህ ረገድ በፈጠራ ስራዎች ላይ ተግቶ በመስራት ፤ውጤታማ በሆኑ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ፤በፈጠራ ስራው ላይ ተሳታፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎችን በማፍራት የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል:: በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ አለን!