ማስታወቂያ

National Exit Model Examination Schedule

National Exit Model Examination Schedule of Examinees assigned in Wolkite University. Students who need account activation can go to Central Library starting from tomorrow  morning

Read more ...

ማስታወቂያ

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባቹህ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፣

Read more ...

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ማለፋችሁን ያረጋገጣችሁ

Read more ...

 

ስልጠናው Standards & Procedures for Lab Accreditation and Calibration የሚለውን ርዕስ መሰረት አድርጎ የሚሰጥ ሲሆን የስልጠናው ዋና ዓላማ የሳይንስ ቤተሙከራዎችን በቀጣይ አክሬዲቴሽን ለማግኘት በሚያስችላቸው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚያስችል መሆኑን የስልጠናው አስተባበሪዎች ገልጸዋል::

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት በተቋማዊ የስልጠናና ጥራት ማሻሻያ አስተባባሪ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አብረሀም ሙላቱ ሲሆኑ እሳቸውም በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንደገለጹት ስልጠናው በቀጣይ ላቦራቶሪዎቻችንን የሚፈለገውን የተስማሚነት ምዘና አሟልተው በአንድ በተወሰነ ደረጃ በሚዘጋጀው መስፈርት ተለይተው የሚፈለገውን ስታንዳርድ ማሟላታቸው ሲረጋገጥ ብቃታቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ለማግኘት እንዲያስችል እንደ ተቋም አስቀድመን ማሟላት የሚገባንን መስፈርቶች ምን ምን እንደሆኑ እና ለአክሬዲቴሽን የሚያስፈልጉ ስታንዳርዶችን ከወዲሁ ለመለየት የሚረዳና አስፈላጊውን ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የስልጠና ፕሮግራም መሆኑን ጠቅሰው ከስልጠናው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንጻር ሰልጣኞች ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉ አሳስበዋል::

ስልጠናውን የሚሰጡት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ አክሬዲቴሽን ጽ/ቤት የመጡ ባለሙያዎች ሲሆኑ በስልጠናው ላይ የሚካፈሉት 80 ሰልጣኞች በሶስት የስልጠና ቦታዎች ላይ ተከፋፍለው በኢንስፔክሽን ፣በሜዲካል(ህክምና) እና በፍተሻ(ቴስቲንግ) ዘርፎች ስልጠናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል:: በተጨማሪም ከአሰልጣኞቹ መረዳት እንደተቻለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አክሬዲቴሽን ጽ/ቤት የተለያዩ ደረጃዎችን መሰረት አድርጎ የተለያዩ የአክሬዲቴሽን አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በዚህ ስልጠና ላይ ትኩረት የሚደረግባቸው ዘርፎች :-

በፍተሻ ላቦራቶሪ :-ደረጃው ISO/IEC17025:2017

በህክምና ላቦራቶሪ :-ደረጃው ISO15189:2012

በኢንስፔክሽን :-ደረጃው ISO/IEC17020:2012 ሲሆኑ አጠቃላይ ስታንዳርዱን አስመልክቶ በቂ የሆነ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችል ስልጠና እንደሚሰጥ አሰልጣኞቹ በስልጠናው የመጀመሪያ ክፍል ላይ ገልጸዋል ::

ከዚህም በተጨማሪ ለተስማሚነት ምዘና በዩኒቨርሲቲው የሚገኙት የሳይንስ ላቦራቶሪዎች አግባብነት ባላቸው ዓለምአቀፋዊ መስፈርቶች መሰረት ተመዝነው የአክሬዲቴሽን አገልግሎት እንዲያገኙ፣ ሰልጣኞቹ ከአክሬዲቴሽን ጋር እንዲተዋወቁ፣ በአክሬዲቴሽን ደረጃዎች (Standards) ፣ በአሰስመንት ስልቶችና ተዛማች በሆኑ መስፈርቶች ላይ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው የአሰራር ስልቶችን ከመከተል አንጻር በቂ የሆነ ግንዛቤን ለመፍጠር ታስቦ የተጋጀ ስልጠና መሆኑን አሰልጣኞቹ በስፋት ገልጸዋል::

ስልጠናው የባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ፣ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች የሚገኙትን ላቦራቶሪዎች የአሰራር ቁመና በማሳደግና ዓለም አቀፋዊ ተስማሚነት ወዳለው አሰራር በማምጣት ረገድ ሚናው ዘርፈ ብዙ እንደሆነ ጭምር ተገልጿል ::

ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ መሆኑን ካዘጋጆቹ ለማወቅ ተችሏል::