በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በክረምት መርሀ-ግብር ትምህርታችሁን ለምትከታተሉ ነባር

 

  1. የተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ
  2. የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እና
  3. የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ የትምህርት ክፍል ተማሪዎች በሙሉ :-

በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በክረምቱ መርሀ-ግብር በቱቶሪያል የሚሰጡት የትምህርት አይነቶች ምዝገባ እና የመማሪያ ሞጁሎች ስርጭት ከግንቦት 16-25/2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ የሚካሄድ መሆኑን አውቃችሁ ከላይ በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በየትምህርት ክፍላችሁ በአካል በመቅረብ ምዝገባ በማካሄድ የመማሪያ ሞጁሎችን እንድትወስዱ ስንል እናስታውቃለን::

ማሳሰቢያ፥

በተለያዩ ድርጅቶች ስፖንሰር የተደረጋችሁ ነባር ተማሪዎች የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ በተጨማሪነት ይዛችሁ እንድትቀርቡ እየገለጽን ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና የርቀት ት/ት ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት