የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን  የሪሚዲያል (REMEDIAL)  ትምህርት ፈላጊዎችን ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

 

ስለሆነም በሳምንት መጨርሻ መርሃ ግብሮች በማህበራዊ እና ተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ማመልከት የምትፈልጉ አመልካቾች የካቲት 22 - 29 /2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን  እንገልፃለን።

ማሳሰቢያ

  • በሪሚዲያል ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲው ኃላፊነት ተማሪዎችን አስተምሮ ማስፈተን ብቻ ይሆናል፡፡
  • በሪሚዲያል ፕሮግራም ጨርሰው ካጠናቀቁ በኃላ በቀጣይ ሁኔታዎች ላይ ተማሪዎች የራሳቸውን አማራጭ ይወስዳሉ፡፡
  • በቂ የተማሪ ቁጥር በማያመለክቱባቸው ዘርፎች ላይ ዩኒቨርሲቲው ፕሮግራሙን እንደማያስጀምር እንገልጻለን፡፡

አመልካቾች ለምዝገባ በሚመጡበት ወቅ

  1. ኦሪጅናል ት/ት ማስረጃ (ማለትም የ8፣ 10 እና የ 12ተኛ ክፍል) ከ የማይመለስ ኮፒ ጋር
  2. የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 50 (ሃምሳ ብር ብቻ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ገቢ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000 149 251 368 ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው እናሳውቃለን፡፡
  3. የማመልከቻ ቦታ
  • በ ወልቂጤ መማር ለሚፈልጉ በ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ሬጅስተራር ጽ/ቤት
  • ለቡታጅራ ካምፓስ (ማዕከል) አመልካቾች ምዝገባው በ ቡታጅራ ቴክኒክ እና ሙያ ት/ቤት ውስጥ በሚገኘው ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማስተባብሪያ ቢሮ

                                                             የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጅስትራር ዳይሬክቶሬት