ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነባር ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ

 

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም ለሁሉም የዩኒቨርሲቲው ነባር ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች የትምህርት ምዝገባ የሚከናወነው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

  1. ሁሉም ነባር ሶስተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ቅድመ ምረቃ እንዲሁም አዲስና ነባር የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 28 እና 29/2015 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በየኮሌጃችሁ ሬጅስትራር በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
  2. ነባር አንደኛ ዓመት ( Freshman) ተማሪዎች የትምህርት ክፍል ምደባ ገለጻ (Orientation) የሚሰጠው ጥቅምት 28/2015 ዓ.ም ሲሆን ወደ ትምህርት ክፍል መግቢያ ፈተና ጥቅምት 29/2015 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ ፡-

ይህንን የመግቢያ ጊዜ አሳልፎም ሆነ ቀድሞ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

                                                       የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

Copyright © 2024. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT