Slide 1

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 2

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 3

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 4

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 5

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 6

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 7

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 8

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 9

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 10

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 11

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 12

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 13

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 14

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 15

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 16

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

Slide 17

Wolkite University

We Strive for Wisdom!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት ስድስት ዓመታት ተቋሙን በፕሬዝዳንትነት ለመሩት ለዶ/ር ፋሪስ ደሊል የእውቅናና የምስጋና፣ እንዲሁም ለአዲሱ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብደልሙህሲን ሃሰን የእንኳን ደህና መጣህ መርሃ ግብር በደመቀ ሁኔታ አካሄደ።
በዚሁ የሽኝትና የቅበላ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር አብደልሙህሲን ሃሰን፤ ተቋሙ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልየታ ውስጥ በተግባራዊ ሳይንስ ዘርፍ መመደቡን አስታውሰዋል። 
ዩኒቨርሲቲው የተጣለበትን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የሚያስችለውን የአስር ዓመት ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝና በአሁኑ ወቅትም ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። 
"ዩኒቨርሲቲው በመማር-ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፎች በርካታ ስኬታማ ተግባራትን እየተከናውነ ይገኛል።" - ዶ/ር አብደልሙህሲን ሃሰን (የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት) 
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል በነበራቸው የስድስት ዓመታት የአመራር ቆይታ ተቋሙ በተለያዩ ዘርፎች ጉልህ ስኬቶችን እንዲያስመዘግብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን በምስጋና አውስተዋል። 
የፕሮግራሙ የክብር እንግዳ የነበሩት የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እና የኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው፤ ዶ/ር ፋሪስ ደሊል በአመራር ዘመናቸው ላስመዘገቡት ስኬት ያላቸውን አድናቆት ገልጸው፣ በቀጣይ የሕይወትና የስራ ጉዟቸው መልካሙን ሁሉ ተመኝተዋል። 
ኮሚሽነሩ አያይዘውም ለቀድሞውና ለአዲሱ ፕሬዝዳንት ባስተላለፉት መልዕክት፦ 
• ተቋሙ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የጀመሩትን የልማት ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ፤
• የተጣሉትን ጠንካራ መሠረቶች በመጠቀም ዩኒቨርሲቲውን ወደ ላቀ ስኬት ለማሸጋገር ሁሉም አካላት በትብብር መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
• የስራ አመራር ቦርዱም ተቋሙን ለማሳደግና ለመደገፍ አስፈላጊውን እገዛ ሁሉ እንደሚያደርግ በድጋሚ አረጋግጠዋል።
የቀድሞ ፕሬዚደንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል በቆይታቸው ያካበቱትን ጠቃሚ የስራ ልምድና ተሞክሮ ለተሳታፊዎቹ ያካፈሉ ሲሆን፣ ለተደረገላቸው የክብር ሽኝትና እውቅና የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በቆይታቸው የተመዘገቡት ስኬቶች በሙሉ የጋራ ጥረት፣ የቡድን ስራና የቅንጅት ውጤቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል። 
በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የካውንስል አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎች በክብር ተገኝተዋል። 
በመርሃ ግብሩ የዩኒቨርሲቲያችን ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እና የኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ደበሌ ቃበታ፣ የዩኒቨረስቲያችን ፕሬዚደንት ዶ/ር አብደልሙህሲን ሃሰን፣  የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ፐሬዚደንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙስጠፋ ሃሰን፣ የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ሙራድ ከድር፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የጉራጌ ዞን አስተዳደሪ ተወካይ እና  የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ክቡር አቶ ደሳለኝ ገብሬ፣ የካውንሰል አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የሃገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡
በመጨረሻም በዕለቱ በተዘጋጀው በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ  ተካሂዶ መርሃ ግብሩ መቋጫውን አግኝቷል።
ለጥበብ እንተጋለን! 
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት!