የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከሰን ራይዝ ግብርና ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ካምፓኒ ጋር በጋራ ለመስራት ተፈራረመ። የመግባቢያ ስምምነቱን የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል እና አቶ መሃመድ ብሩክ ሰንራይዝን በመወከል ተፈራርመዋል።
በዩኒቨርሲቲው አሰተባባሪነት በዋቤ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ወደ ስራ የሚገባው ሰንራይዝ አዋጪነታቸው በተረጋገጡ የግብርና ምርቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ የሚስሩ ይሆናል።
ስራው ከትርፍ አምጪነቱ ባሻገር ለዩኒቨርሲቲው ቀጥተኛ ዓላማ የሆኑት ለመማር እና ማስተማር፣ በምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ልዩ እገዛ ያደርጋል።
በድርጅቱ አማካኝነት የሚመረተው ምርት ከአካባቢ ፍጆታ የተሻገረ ዓላማ ያነገበ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለስራው ስኬታማነት የግብርና እና ቢዝነስ ባለሙያዎች እገዛ ማድረግ የሚችልበት ሰፊ ዕድል ያለው መሆኑን ዶክተር ፋሪስ በመግባቢያ ስምምነት ስነ ስርዓቱ ላይ ገልጸዋል።
ለጥበብ እንተጋለን!
ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት
Wolkite University signed Memorundum of Understanding with Sunrise Agricultural Business Plc to cooperate for mutual benefit.
The MoU was signed by the President of our University, Dr. Faris Delil and Mr. Mohamed Beruk on behalf of Sunrise plc.
Sunrise enters into operation under the supervision of Wolkite University with Wabe Business and Consulting Enterprise.
The execusion of the project will focus on agricultural products whose contributions are practically proven. Beyond its profit-making, the project provides a unique support teaching and learning, research and technology transfer to result impact on our University vision. The product of the project will be dispatched accross the University catchement and the nation at large.
Dr. Faris stressed at the moment of the signining ceemony of MoU that the project will be assisted by pur Agricultural and Business experts that will add value on the appropriate accomplishmnet of the project to bear impact.
We Strive for Wisdom!
Public and International Relation