በምረቃ ስነ ስርዓቱ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ የበኩር የሆኑ 21 የስፔሻሊቲ ህክምና ትምህርታቸውን በቀዶ ህክምና፣ በውስጥ ደዌ፣ በማህጸንና ጽንስ እና በህጻናት ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ ሀኪሞችን አስመርቋል።
በተጨማሪም በመደበኛ እና ተከታታይ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም 417 ተማሪዎችን በዛሬው እለት በልዩ ኩነት አስመርቋል።
የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል በምረቃ ስነ ስርዓቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ አቀፍ ብልፅግና ለማስመዝገብ እንዲያስችላት እና ከቀሪው ዓለም ጋር ተወዳዳዳሪ እንድትሆን የትምህርት ልማት ስራ የማይተካ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም በዩኒቨርሲቲያችን የከፍተኛ ትምህርት ሪፎርም ትግበራ ውጤታማነት ማሳያ የሆነው የዘንድሮ ዓመት የመውጫ ፈተና ውጤት 98% መመዝገቡ የሚበረታታ በመሆኑ በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጠበቀ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የዩኒቨርሲቲያችን ስራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ እና የእለቱ የክብር እንግዳ ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ተመራቂዎች የዛሬ የምረቃ ቀናቸው ታላቅ አደራ እና ኃላፊነት የሚቀበሉበት እለት እንደሆነ አውስተዋል። ፕሮፌሰር ጌትነት እንዳሉት ተመራቂዎች ዛሬ የደረሱበትን ስኬት እንደ መሰላል በመጠቀም ሙያቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው አጥብቀው ጥይቀዋል።
በዕለቱ የሴቶች የመብት ትግል ፋና ወጊ በሆነችው የቃቄ ውርድወት የዩኒቨርሲቲው የመመረቂያ አዳራሽ በስሟ ተሰይሞ ስራውን በይፋ ጀምሯል።
በመጨረሻም ተማሪ አቡጎሽ ተስፋዬ ከህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከሜዲካል ላቦራቶሪ ሳይንስ ትምህርት ክፍል 3.95 ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የዋንጫ እና ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነ ሲሆን ከህክምና ትምህርት ቤት ዶክተር ዮሐንስ ምንአለ 3.83 ውጤት ያስመዘገበ በመሆኑ የሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።
በመጨረሻም ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ተጠናቋል።
ዩኒቨርሲቲያችን ለተመራቂዎች በድጋሚ እንኳ ደስ አላችሁ በማለት መልካም ምኞቱን እየገለጸ፤ ተመራቂዎች በህይወት መንገዳችሁ መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማችሁ እና ስኬታማ የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ ይመኛል!
የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት
In the 16th Round Graduation 21 Specialist Doctors were graduated
____
Saturday, March 28, 2026 (WKU)
Wokite University held its 16th round Graduation Ceremony. At the graduation ceremony, 21 Specialist Doctors were graduated in the history of the University in Surgery, Internal Medicine, Gynecology and Pediatrics.
Three hundred ninty six students have been attending their education in Undergraduate and Master's degree as well as in Speciality Program are graduated today.
The President of our University, Dr. Faris Delil, delivered a congratulation message at the Inauguration ceremony.
He stated that the work of educational development has an irreplaceable role in enabling Ethiopia to achieve out wholistic growth and become competitive with the rest of the world.
The President has passed a strong message on the continuity of 98% exit exam results registerd as it was encouraging factor.
The Governing Board of Our University's Vice Chairperson and Honorable Guest of the day, Professor Getenet Tadele, deliverd a congratulation message and have indicated that today's graduation day has to be the day they receive the greatest responsibility.
He also insiated the graduates
to increase their careers using the current success they have achieved as a ladder.
The University Graduation hall officially named by the Iron laddy women's rights fighter,YeKakie Weredewet.
A student by the name Abugosh Tesfaye from the College of Medicine and Health Science from the Medical Laboratory Science Department was awarded the Trophy and Medal with the highest Score of 3.95, and Doctor Yohannes Menale from School of Medicine was awarded the medal as he had scored 3.83.
Finally, the National Anthem of Ethiopia has been used at the last stage of the Ceremony.
Our University expressses its best wishes to graduates.
Public and International Relation
To know more about us, please