የዩኒቨርሲቲውን ሠራተኞች በተለይም የሴቶችን ድርብ የኃላፊነት ሸክም የሚያቃልለው ፣ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ውስጥ የተገነባው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች የሕጻናት ማቆያ ማዕከል እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ ተመርቋል፡፡ በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ክቡር ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ፣ ክቡር ዶክተር ፋሪስ ደሊል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት፣ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ክቡር አቶ ሺሰማ ገብረ ሥላሴ የጉልባማ የቦርድ ሰብሳቢ፣ ክቡር አቶ ኤልያስ ሽኩር የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የዩኒቨርሲቲው የሴኔት አባላት ተገኝተዋል፡፡
ለጥበብ እንተጋለን!
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት