የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ከተቋቋመበት ከ 2004 ዓ/ም ጀም ወደ 13 የሚሆኑ ዘርፎችን አዋቅሮና ከስሩም ብዙ ንዑሳን ኮሚቴዎችን አደራጅቶ በየሳምንቱ ከዘርፍ ተወካዮች በየ 15 ቀኑ ከንኡሳን ኮሚቴዎች እና ከቅርንጫፍ ጊቢ የተማሪ ህብረት ተወካዮች ጋር እንዲሁም ደግሞ ከ አጠቃላይ የክፍል ተወካዮች የፓርላማ አባላት ጋር በየ3 ወሩ ስብሰባ በማድግ እና ፓርላሜንተሪ ስርዓት ይዘን መጓዝ ከጀመረ አእነሆ 4 ዓመታት ጥር ነው፡፡

በነዚህ ሁሉ ጊዜያት የጊቢው የመማር ማስተማር ሂደት ፍጹም ሰላማዊ በተግባር የተደገፈ እና የሴቶችን ቲቶሪያል ድጋፍን ያማከለ እንዲሆን በቁርጠኛ አቋም ተግቶ እየሰራ ይገኛል ፡፡ከዚህም በጠጨማሪ በዩኒቨርሲቲያችን ያሉ ተማሪዎች በስነ ምግባር የታነፁና አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን በመስራት የራሳቸው ችሎታ የሚያዳብሩ የዩኒቨርሲቲያቸውንም መልካም ገጽታ የሚገነቡ ለችግሮቻቸው ሌላ አካል መፍትሄ  እንዲሰጣቸው የሚጠብቁ ሳይሆን ችግር ፈቺ የልማት እና የለውጥ አርአያ ለዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ፤ለሀገራችን ፤ለህዝባችን እድገት ትልቅ ሚና የሚጫወጡ እና የህዳሴውን ጉዞ ለማስቀጠል ታሪክ ነጋሪ ሳይሆን ታሪክ ሰሪ ተተኪ ትውልድን በማፍራቱ ረገድ ህብረቱ ከዩኒቨርሲቲው ጋር አብሮ በመሆን እየሰራ ይገኛል፡፡

ራዕይ

በ 2020 በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ የተማሪዎች ህብረት መካከል አንዱ ሆኖ መገኘትና በኢትዮጲያ በ5 ዓመት ውስጥ አንደኛ የተማሪዎች ህብረት በመሆን በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ደግሞ ከአለም የተማሪዎች ህብረት ውስጥ ከ100 ምርጥ የተማሪዎች ህብረት አንዱ ሆኖ መገኘት፡፡

አላማ

የተማሪዎቸን ሁለንተናዊ ቸግር መፍታት፤ በዩኒቨርሲቲ ቆይታው በዕውቀት፤በክህሎትና በሙያው ቸሎታ እንዲሁም ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር በመልካም ስነ-ምግባር የታንጹ ዜጎች እንዲሆኑ ማመቻቸት፡፡

ተልዕኮ

ለተማሪዎች ሰላማዊ የሆነ የመማር ማስተማሩ ስራው እንዲሰፍን ለማድረግ በትምህርት ልቀት ፤በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት የጎለበተ አግባብነት ጥራት ያለው እውቀት የጨበጠ ተማሪ እንዲሆን ማመቻቸት፡፡

እሴቶች

  • አገልጋይነት
  • ፍትሐዊነት
  • ተባባሪነት
  • ግልፅነት
  • ቁርጠኝነት

አሳታፊነት  

በህብረቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት  የሚመረጥ አንድ የተማሪዎች ህብረት የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ነው፡፡ ሆኖም በድጋሚ ሊመረጥ ይቻላል፡፡ ህብረቱ 16 አባላት ያሉት ሲሆን እነዚህም 1 ፕሬዚዳንት፣ 1 ም/ፕሬዚዳንት፣ 1 ፀሐፊ እና 13 ስራ አስፈጻሚዎች ይዞ  ስራውን በተቀላጠፈ መልኩ ይወጣል፡፡

 

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ስር ስራ ሶስት ዘርፎች እና 16 ክበባትና ማህበራት ይገኛሉ፡፡

የክበባት ስም ዝርዝር

  1. ሸጋ ፌስት ክበብ
  2. ሊቭ ፎር ጀነሬሽን ክበብ
  3. ፀረ-ኣድስ ክበብ
  4. ኢንቫሮመንታል ክበብ
  5. የአቻ ለአቻ ምክክርና የስነተዋልዶ ክበብ
  6. ፃታዊ ትንኮሳን መከላከል ክበብ
  7. ሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ
  8. እንግሊዘኛ ቋንቋ ክበብ
  9. ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ክበብ
  10. ቀይ መስቀል
  11. ፍቅር በህይወት ክበብ
  12. ባዮ-ቴክ ክበብ
  13. ሳይኮሎጂ ክበብ

ሲሆኑ ሁሉም ክበባት ተማሪዎችን በአባልንነት በመያዝ ተማሪዎች ጌዜያቸውን በአልባሌ ነገሮች እንዳያሳልፉ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡

    የማህበራት ስም ዝርዝር

  1. የሲቪል ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር
  2. የሶፍትዌር ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር
  3. የአርክቴክቼር ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር
  4. የመካኒካል ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር
  5. የኤለክትሪካል እና ኮምፒተር ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር
  6. የኮንስትራክሽን እና ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር
  7. የሲቪክ ተማሪዎች ማህበር
  8. የኢንፎርሜሽን ሲስተም ተማሪዎች ማህበር
  9. የአኒማል ፕሮዳክሽን እና ቴክኖሎጂ ተማሪዎች ማህበር
  10. የውሃ ሀብት ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር
  11. የአካውንቲንግ ተማሪዎች ማህበር

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ክበባትና ማህበራት ተጠሪነታቸው ለተማሪዎች ህብረት ሲሆን የተቋቋሙ ክበባትና ማህበራት ዓላማቸውን ለማሳካት ፈቃደኛ ተማሪዎችን በአባልነት በመመዝገብ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ለዚህም ስኬት ዓመታዊ እቅዳቸውን ለተማሪዎች ህብረት አቅርበው ያስጸድቃሉ፤ በየሩብ ዓመቱ ማጠናቀቂያ ሪፖርት ያቀርባሉ፤ በተማሪዎች ህብረት እና በተማሪዎች ዲን አማካይነትም እገዛ፣ ድጋፍና ክትትል ይደረግላቸዋል፡፡

Copyright © 2024. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT