ማስታወቂያ
ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በ2011 የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሳምንቱ መጨረሻ የእረፍት ቀናት /ቅዳሜና እሁድ/ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የመግቢያ መስፈርት መሰረት አዲስ ተማሪዎችን በድህረ-ምረቃ ትምህርት ፕሮግራም፡-
በወልቂጤ፣ ቡታጅራ እንዲሁም ከግሪን ምርምርና ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ በከፈትነው ካምፓስ ከሃምሌ 15/2011 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡
በመሆኑም መስፈርቶችን የምታሟሉ አመልካቾች የዩኒቨርሲቲው ዋናው ሬጅስትራር ፅ/ቤት ወደፊት በሚያሳውቀው የምዝገባ ጊዜ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
‹‹ለጥበብ እንተጋለን!››