ድጋፉ የተደረገው በጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ በኩል ከየወረዳ ለተለዩ ድጋፍ ለሚሹ 500 ተማሪዎች፣ በወልቂጤ ከተማ ወጣቶች በጎ አድራጎት አማካኝነት ድጋፍ ለሚሹ 80 ተማሪዎች፣ በጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ በኩል ድጋፍ ለሚሹ 40 ተማሪዎች በአጠቃላይ ለ620 ተማሪዎች 3720 ደብተር እና 1900 እስክሪፕቶ ድጋፍ ተደረጓል፡፡ በድጋፍ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ገብሩ እንደገለጹት ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከሚያከናውናቸው በርካታ የማኅበረሰብ አገልግሎት ስራዎች መካከል የክረምት በጎ ተግባራት አካል የሆነው ይህ ድጋፍ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዳይርቁ እና በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዛቸው መሆኑን ጠቁመው መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡