ክፍት የሥራ ቦታ

ማስታወቂያ

National Exit Model Examination Schedule

National Exit Model Examination Schedule of Examinees assigned in Wolkite University. Students who need account activation can go to Central Library starting from tomorrow  morning

Read more ...

ማስታወቂያ

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባቹህ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፣

Read more ...

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ማለፋችሁን ያረጋገጣችሁ

Read more ...
















 

በጀፚረ ቅርስ አጠባበቅ ዙሪያ በሀገር በቀል ዕውቀት ልማት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀው የምክክር መድረክ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡ “ጀፚረን የመሰሉ እንቁ ቅርሶቻችንን ተንከባክበንና ጠብቀን ለትውልድ እናስተላልፍ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ተወካይ፣የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ፣ የጉራጌ ዞን የሴቶች ወጣቶችና ህጻናት መምሪያ ሀላፊ፣ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ 16 ወረዳዎች የተውጣጡ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሃላፊዎች፣ የጉራጌ የባህል ሸንጎ አባላት እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በምክክር መድረኩ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

የምክከር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል ሲሆን ዶክተር ፋሪስ በንግግራቸው ላይ እንደገለጹት ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት አካል በሆነው የሀገር በቀል ዕውቀት ላይ ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸው በጥናትና ምርምር ተለይተው ከሚሰሩ የማህበረሰብ አገልግሎቶች አንዱ የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ስራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ዶክተር ፋሪስ አያይዘውም የጉራጌ ማህበረሰብ እንደሌሎች የሀገራችን ህዝቦች ሁሉ የአኩሪ ባህል ባለቤት መሆኑን አስታውሰው ከእነዚህም አኩሪና ከሚዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች መካከል አንዱ ጀፚረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ጀፚረ ከዘመናዊ ምህንድስና የማይተናነስ በመንደሮች መካከል የሚያልፍ ግርማ ሞገስን የተላበሰ ጥበብ መሆኑን ዶክተር ፋሪስ በንግግራቸው ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዶክተር ፋሪስ እንደገለጹት በጉራጌ ታሪክ ጥንት መሬት የሚከፋፈለው በዘፈቀደ ሳይሆን በባህሉ በተመረጡ አባቶች እና የመሬት ልኬት ዳኞች አማካይነት መሆኑን ገልጸው “ጎጎት” መጽሀፍን ዋቢ በማድረግ እንደገለጹት ጀፚረ ስፋቱ12 ዘንግ መሆኑንና ርዝመቱ ግን በመሀል የሚያልፍ ወንዝ ፣ ገደል ወይም ደን እስከሌለ ድረስ ሳይቋረጥ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ዶክተር ፋሪስ በተጨማሪ እንደገለጹት ጀፚረ የለቅሶ ስርዓት የሚፈጸምበት፣እግረኛና ፈረሰኛ ሙሾ የሚደረድርበት፣የሰርግ ስነስርዓት ሲኖር የሙሽሪትና የሙሽራ አጃቢ ወገኖች በዘፈንና በግጥም የሚሞጋገሱበትና በሽማግሌዎች የሚባረኩበት፣ሙሽሮች አጋጌጣቸው የሚታይበትና ውበታቸው ጎልቶ የሚወጣበት፣በእናቶችና አባቶች የሚመረቁበት፣ሕጻናት እንዳሻቸው የሚቦርቁበት ፣ ጎረምሶች የገና ጨዋታ የሚጫወቱበት፣ ዳመራ የሚደመርበት፣ወጣቶች የፈረስ ጉግስ የሚለማመዱበት፣ በቅሎና ፈረስ የሚገራበት፣ኮርማዎች እርስ በርሳቸው የሚፈታተሹበትና የሚያጓሩበት እንዲሁም ሽማግሌዎች ባህላዊ ዳኝነት የሚያካሂዱበት መሆኑን በዝርዝር ገልጸዋል፡፡ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲም ለዚህ ታሪካዊ ቅርስ ትልቅ ቦታ በመስጠት ጀፚረ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን እንዲያገኝ በማሰብ ፡-

1ኛ) በዩኒቨርሲቲው ማስተር ፕላን ላይ ጀፚረ በዲዛይን መካከተቱን

2ኛ) ጀፚረንዳ በሚል ስያሜ በወልቂጤ ኤፍ ኤም 89.2 ሬዲዮ በሳምንት ሁለት ቀን የሚተላለፍ ፕሮግራም መጀመሩን

3ኛ) በቀጣይ ዓለም አቀፍ ስርጭት ሊኖረው የሚችል “ Jofere Ethiopian Journal of Applied Sciences” የሚል የጆርናል ህትመት ለማስጀመር በዩኒቨርሲቲው ሴኔት መጽደቁን

4ኛ) የዩኒቨርሲቲው ሎጎ ሙሉ በሙሉ ጀፚረን የሚገልጽ መሆኑን ዶክተር ፋሪስ በዝርዝር ገልጸው ይህ እንቁ የሆነው ቅርስ ለተለያዩ ሰው ሰራሽ አደጋዎች መጋለጡን በማስታወስ ይህንን መነሻ አድርጎ ዩኒቨርሲቲው የምክክር መድረኩን ማዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ ከዶክተር ፋሪስ ደሊል የመክፈቻ ንግግር በኋላ “Tracing Jefore’s Features, Provisions, intervention and Restoration” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሁፍ በዩኒቨርሲቲው የSociology ትምህርት ክፍል መምህር በሆኑት በመምህር አብነት ሺፈራው የቀረበ ሲሆን በቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ ሰፋ ያሉ ውይይቶች ተካሂደውበታል፡፡

በምክክር መድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደተገለጸው ጀፚረ እጅግ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ ላይ ስለሚገኝ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ሊደረግለት እንደሚገባ፣ የጉራጌ ማህበረሰብ የጀፚረ ባለቤት ስለሆነ ጀፚረን ሊንከባከበው እንደሚገባ፣ የባህል ሸንጎ አባላቶቻችን በትኩረት መስራት እንዳለባቸው፣የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ በመሆን ጀፚረን በባህላዊ ቅርስነት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት ቢደረግ፣ለጀፚረ ዕውቅና ሊሰጠው እንደሚገባ፣ ጀፚረን በተስተካከለ መንገድ እያቆዩ ያሉት የማህበረሰብ ክፍሎች ዕውቅና ቢሰጣቸው፣ ለጀፚረ የይዞታ ማረጋገጫ ቢዘጋጅለት፣ በጀፚረ ላይ ጥናቶች በስፋት ቢሰሩ፣ የህግ ማዕቀፍ ቢዘጋጅለት፣መንገድ ሲሰራ ዲዛይኑ ላይ የጉራጌ ባህላዊ ሸንጎ አባላት እንዲሳተፉና አስተያየት እንዲሰጡ ቢደረግ፣ መዋቅራዊ ጥበቃ ቢደረግለት፣ መሰረተ ልማቶች ሲገነቡ ቅንጅታዊ አሰራሮች ቢፈጠሩ የሚሉና ሌሎችም አስተያየቶች በምክክር መድረኩ ላይ ተነስተዋል፡፡ በመጨረሻም የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች በቸሀ ወረዳ፣ በፈረዝዬ ቀበሌ አንዛናባጥ በተሰኘ መንደር ተገኝተው የችግኝ ተከላ አከናውነዋል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ 13ኛ ዓመት አስመልክቶ “ የዓባይ ዘመን ትውልድ “ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የስነ-ጽሁፍ ፕሮግራም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

Read more ...

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት አባላት የዋቤ የንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ የፈረዝየ የአቮካዶ እርሻን እና የምርምር ጣቢያ የስራ እንቅስቃሴዎችን ጎበኙ።

Read more ...

በ2016 የትምህርት ዘመን ለማማካሻ ትምህርት (Remedial) ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡት ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ወደ ተቋሙ መግባት ጀምረዋል

Read more ...

Public Lecture has been held at Wolkite University

Read more ...

በ2015 ዓ.ም. በመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ኮሌጆችና የትምህርት ክፍሎች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ባለድርሻ አካላት እውቅና ተሰጠ

Read more ...

“የባህር በር ጥያቄ የፖለቲካ ወይስ የህልውና ጥያቄ ? “ በሚል ርዕስ ላይ ያተኮረ ሴሚናር በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

Read more ...

ዩኒቨርሲቲያችን በአገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የአቪዬሽን ኢኖቬሽን ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እያከናወነ ያለውን ተስፋ ሰጪ ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት የትምህርት ሚኒስቴር የሱፐርቪዢን ቡድን አሳሰበ

Read more ...

Announcement for Test Takers of National Graduate Admission Test (GAT)

Read more ...

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የካውንስል አባላት በዩኒቨርሲቲው የ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ተወያዩ

Read more ...

የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በመገምገም ላይ ይገኛሉ

Read more ...

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የጨቅላ ሕጻናት የእንክብካቤ ማዕከል እና የመምህራን መኖሪያ በሆነው አፓርታማ ግቢ ውስጥ የሚገኘው ሞዴል የማህበረሰብ መድሃኒት ቤት በይፋ ተመረቁ

Read more ...

በ2014 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ለመተግበር በዋቤ ችግኝ ጣቢያ የተዘጋጁት ችግኞችን አስመልክቶ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የስፔሻሊቲ የትምህርት ፕሮግራሞችን መስጠት ጀመረ

Read more ...

We have 756 guests and no members online

Wolkite University, P.O.Box 07, Wolkite, Guragie Zone, SNNPR, Ethiopia | +251-113-220042 | pird@wku.edu.et/president@wku.edu.et

Copyright © 2024. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT