“MARY HELP COLLEGE SALESIAN SISTERS ETHIOPIA” በፋሽን ኢንዱስትሪው ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው ኮሌጅ ሲሆን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ስር ከሚገኙት ከጋርመንት፤ ከፋሽን ዲዛይንና እና ከቴክስታይል ትምህርት ክፍሎች ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በኩል የፈረሙት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ዮሐንስ ገብሩ ሲሆኑ በ“MARY HELP COLLEGE SALESIAN SISTERS ETHIOPIA” በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የኮሌጁ ዲን የሆኑት Maria Nieves Crespo ናቸው፡፡ በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክተር የሆኑት ረ/ፕ አበበ ያበኬር እንደገለጹት ስምምነቱ በዕውቀት ሽግግር፤ በተማሪዎች ኢንተርንሺፕ እና በመምህራን ኤክስተርንሺፕ ላይ የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡ ስምምነቱ ለሶስት አመት የሚቆይ መሆኑን ከስምምነቱ ሰነድ ለመረዳት ተችሏል፡፡