ክፍት የሥራ ቦታ

ማስታወቂያ

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ማለፋችሁን ያረጋገጣችሁ

Read more ...

የተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ

በ2015 ዓ.ም  የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች

Read more ...

ለሁለተኛ ዙር GAT(Graduate Admission Test) አመልካቾች

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሁለተኛ ጊዜ የብሔራዊ  የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) በሚከተሉት መርሃ-ግብሮች ለመስጠት ቀጠሮ መያዙን አስታውቋል።

Read more ...

 

የዩኒቨርሲቲው የሴቶች ህጻናት እና ወጣቶች ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ከተማሪዎች ህብረት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ112ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ47ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች-8) “ፈጠራና ቴክኖሎጂ ለጾታ እኩልነት” በሚል መሪ ቃል በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ተከብሯል፡፡

ፕሮግራሙን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው የሴቶች ህጻናት እና ወጣቶች ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ መሰረት አስራት ቀኑን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶች መብት መከበር ከመጀመሩ በፊት በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ የሴቶች መብት ተሟጋች የነበረችው የቃቄ ውርድዎት ለሴቶች መብት መከበር ታደርግ የነበረውን ትግል እና የነበራትን ሚና አስመልክተው ለታዳሚዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡

ዳይሬክተሯ አያይዘውም ሴት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እንዴት መፍታት እንደሚችሉ የሚያግዙ የተለያዩ ስልጠናዎች እየተሰጣቸው እንደሚገኝ አስታውሰው ከመደበኛ የትምህርት ሰዓታቸው ውጪ የሚኖራቸውን ጊዜ ወደ ዜሮ ፕላን ማዕከል በመሄድ እንዲያሳልፉና የተለያዩ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን የሚለዋወጡበትን መድረክ በአግባቡ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርት የሆኑት መምህርት እስከዳር ተመራቂ ተማሪዎች በሚኖራቸው የመውጫ ፈተና( EXIT EXAM) ዙሪያ ለታዳሚዎቹ ሰፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በዕለቱም ከ8 ኮሌጆች እና ከ1 ትምህርት ቤት ከየትምህርት ክፍላቸው አብላጫ ውጤት ላመጡ ሴት ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተቋሙ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም ሴት ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ በመገንባት ላይ ያለው የህጻናት ማቆያ በፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ተጎብኝቷል፡፡

ለጥበብ እንተጋለን!

We Strive for Wisdom!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በመገምገም ላይ ይገኛሉ

Read more ...

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የጨቅላ ሕጻናት የእንክብካቤ ማዕከል እና የመምህራን መኖሪያ በሆነው አፓርታማ ግቢ ውስጥ የሚገኘው ሞዴል የማህበረሰብ መድሃኒት ቤት በይፋ ተመረቁ

Read more ...

በ2014 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ለመተግበር በዋቤ ችግኝ ጣቢያ የተዘጋጁት ችግኞችን አስመልክቶ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የስፔሻሊቲ የትምህርት ፕሮግራሞችን መስጠት ጀመረ

Read more ...

We have 296 guests and no members online

Wolkite University, P.O.Box 07, Wolkite, Guragie Zone, SNNPR, Ethiopia | +251-113-220042 | pird@wku.edu.et/president@wku.edu.et

Copyright © 2023. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT