ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ለ9ኛው ዙር ባዘጋጀው ብሔራዊ የጥራት ሽልማት ውድድር የ3ኛ ደረጃ የልህቀት ዋኝጫ ተሸላሚ ሆነ፡፡
የሽልማት ሥነሥርዓቱ የኢፌዲሪ ፕሬዝደንት እና የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ የሆኑት ክብርት ሣህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሰት ኃላፊዎች በተገኙበት ጥቅምት 19/2015 ዓ.ም በታላቁ ቤተ-መንግስት የተከናወን ሲሆን ዩኒቨርሲቲችን በመወከል የዩኒቨርሲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል፤ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ሀብቴ ዱላ እና የተቋማዊ ጥራትና አግባብነት ዳይሬከትሩ አቶ ብዙዓለም አሰፋ ተገኝተዋል፡፡
ዘንድሮ በዚህ ውድድር ከተሳተፉ የምርትና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል የ3ኛ ደረጃ የልህቀት ዋንጫ ተሸላሚ ብቸኛው ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ውድድሩን ለየት ያደርገዋል።
በዚህ አጋጣሚ ለዚህ ስኬት መብቃት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱት አካላት፡ ለመጥቀስ ያህል የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እና መስተዳድሩ፣ መንግሰታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም ሌሎች እያመሰገንን ለቀጣይ የላቀ ስኬት አጋርነታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ አደራ እንላለን፡፡
በድጋሚ እንኳን ድስ ያለን!!
ለጥበብ እንተጋለን!