ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሰራኞች በሙሉ
እንደሚታወቀው በዩኒቨርሲቲያችን የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ለመውሰድ ተማሪዎች ከቀን 26/01/2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በመግባታቸው የተነሳ የፈተናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል በዩኒቨርሲቲው ከተፈቀደላቸው ሰራተኞች ውጭ ሌሎች ሰራተኞች ለስራ ወደ ግቢ አለመግባታቸው ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ፈተናው በዛሬው ዕለት በሰላም የተጠናቀቀ በመሆኑ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ሰራኞች በሙሉ ከቀን 14/02/2015 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሁም መምህራን በትምህርት ካላንደሩ መሰረት ከቀን 21/02/2015 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ስራ የሚጀምር መሆኑን አውቃችሁ ከተጠቀሰው ዕለት ጀምሮ በስራ ገበታችሁ ላይ እንድትገኙ ዩኒቨርሲቲው ያሳስባል፡፡