ዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ከ11,000 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በየኒቨርሲቲው ዋናው ካምፓስ ለማስተናገድ ያደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ ከትምህርት ሚኒስቴር የመጡት ሱፐርቫይዘሮች በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ዩኒቨርሲቲው ያደረገውን ቅድመ ዝግጅት ገምግመዋል፡፡
በዚህም መሰረት ገምጋሚ ቡድኑ የተደረገውን አጠቃላይ ዝግጅት በተለይም የመፈተኛ ክፍሎችን ዝግጅት ፣ የተማሪዎች የመመገቢያና የማደሪያ ክፍሎችን፣የመጸዳጃ ስፍራዎችን፣ የህክምና መስጫ ስፍራዎችን፣ የፈተና መከዘኛ ፣ አጠቃላይ የፋሲሊቲ ሁኔታዎችንና የግቢ ደህንነትና ጥበቃ ዝግጁነትን በስፋት ጎብኝተዋል ።
ሱፐርቫይዘሮቹም ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት አጠቃላይ ዝግጅቱ በጣም ጥሩ እንደሆነ እና ባዩት ነገር ደስተኛ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በአፈጻጸም ሂደት ላይ በግልጽ ተለይተው ያልተቀመጡ ተግባራትን አስመልክቶ ከሚመለከተው የትምህርት ሚኒስቴር አመራር ጋር ተወያይተው ምላሽ እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡
እስካሁን ድረስ የተደረገው ዝግጅት በጣም ጥሩ ስለሆነ ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ሱፐርቫይሮቹ አሳስበዋል፡፡