ክፍት የሥራ ቦታ

ማስታወቂያ

National Exit Model Examination Schedule

National Exit Model Examination Schedule of Examinees assigned in Wolkite University. Students who need account activation can go to Central Library starting from tomorrow  morning

Read more ...

ማስታወቂያ

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባቹህ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፣

Read more ...

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ማለፋችሁን ያረጋገጣችሁ

Read more ...
















 

የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ የሚከበረው ከየትኛውም የዓለማችን ክፍል በበለጠና በላቀ ሥነ ሥርዐት ነው፡፡የመስቀል በዓል አከባበር መንፈሳዊነቱንና ባህላዊ ገጽታውን ሳይለውጥ ለዘመናት የቀጠለበት ምክንያት በሕዝቡ ዘንድ በሚገባ እንዲሠርጽ ከመደረጉ አንጻር ይመነጫል።የመስቀል ክብረ-በዓል ሀገራዊ እና አካባቢያዊ መልክ ይዞ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተለያየ ሁኔታ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡

በዓሉ መንፈሳዊ በዓል ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ይህን በዓል የባህላቸው፣ የትውፊታቸው፣ የማኅበራዊ እሴታቸው አካል አድርገው ነው የሚያከብሩት፡፡ የመስቀል በዓል አከባበር ልዩ ሊሆንና የዓለምን ትኩረት ሊስብ የቻለውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡

ይህ ታላቅ በዓል በተለይም የክርስትና ዕምነት ተከታይ የሆኑትን ባህል ፣አኗኗር እና ወግ በተላበሰ መልኩ የሚከበር ቢሆንም የበዓሉ አከባበር ደረጃና የሚሰጠው ትኩረት ከቦታ ቦታ ይለያያል፡፡ በጉራጌ ህብረተሰብ ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩት በዓላት መካከል የመስቀል በዓል ዋነኛው ነው፡፡ የመስቀል በዓል በጉራጌ ትውፊት የጉራጌ ማህበረሰብ ለመስቀል ያለውን የጠለቀ ዕውቀት ያሳያል።

የክብረ-በዓሉ ታሪክና ምንነት ዕይታችንን አስፍተን ስናጤነው ከጉራጌ ህዝብ አንጻር ከበዓላት ሁሉ ልክ ሙስሊሙ የጉራጌ ማህበረሰብ የአረፋን በዓል በተለየ መልኩ እንደሚያከብረው ሁሉ የመስቀል በዓልም ለየት ያለ ምሥጢራዊ ትርጉም ያለው በዓል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በተለመደው አነጋገር "የጉራጌ መስቀር" ወይም "የጉራጌ መስቀል" ትውፊትና የክብረ-በዓሉ አተገባበር ሥርዓት ረጅም ምዕተ-ዓመታት ተሻግሮ እስካለንበት ዘመን የዘለቀና፣

  • • የጥንታዊው የጉራጌ ማህበረሰብ ሀይማኖታዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ስነ-ልቦናዊ አንድነት የሚገለፅበት፤
  • • ጥንታዊ የጉራጌ አባቶች የነበራቸው ምናባዊ ምጥቀት፤ የነበራቸው ጠንካራ የግንኙነት ሥርዓት፤ በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ የነበራቸው መግባባትና በተግባቡበት ነገር ላይ የነበራቸው የአተገባበር ብልሀት፤ የነበራቸው የህዝብ አደረጃጀትና አመራር ጥበብ ወዘተ….የመሳሰሉትን በምናባችን ወደኋላ መለስ ብለን የእነሱን ልምድ እንድናስብና እንድንማማርባቸውም ቀደምት አባቶቻችን በአሻራቸው አፅንተው የተዉልን ፈርጀ-ብዙ ቅርስ ነው ቢባል አልተጋነነም፡፡

በጉራጌዎች እምነት ደመራ ከተተከለበት ከነሐሴ 12 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 5 ቀን ድረስ የእፎይታ ጊዜ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ጥንታውያኑ የጉራጌ አባቶች ማንኛውም ሰው የመስቀል በዓልን ነፃና ሰላማዊ በሆነ መንፈስ እንዲያከብር ለማስቻል በነዚህ ቀናት የሚተገበሩ የተለያዩ ደንቦችን ደንግገዋል፡፡ ይኸዉም:-

  • • የመስቀር በዓል የሰላም፣ የእፎይታ፣ የመቻቻል፣ የፍቅርና የደስታ በዓል እንደሆነ በጥንታዊ አባቶች እምነት መስቀር ደስታን ይወዳልና ማናቸውም ነገሮች የሰውን ደስታ ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ መፈጸም እንዳለባቸው፤
  • • ማንኛውም ሰው በዚህ ወቅት መጨናነቅ እንደሌለበት እና ገንዘብ መበደር ወይም ማበደር ቢቻልም እዳ እንዲመለስ መጠየቅ ግን እንደማይቻል፤
  • • በዚህ ወቅት የቤት ደጋፊ ሠራተኛን መቅጠር እንጂ ከሥራ ማፈናቀል እንደማይፈቀድ፤
  • • በመስቀር ጋብቻ እንጂ ፍቺ የማይፈቀድ መሆኑ እና ባልና ሚስት ቢጣሉ እንኳ “እስኪ በዓሉን አሳልፋችሁ በሽማግሌ ይታይ” በሚል እርቅ የሚወርድ መሆኑ፤
  • • በመስቀር ሰላም፣ ፍቅር፣ መቻቻል እንጂ ጥል፣ ክርክር፣ ሀሜት ወይም በዚህ ምክንያት የሚደረግ ሙግት ሊያስነሳ የሚችል የእርቅ ሽምግልና እንኳን እንዲኖር አይፈቀድም፡፡ ምክንያቱም በመስቀል በዓል ወቅት ጸብ የሚጭር ሰው በበዓል ወቅት ይሞታል ተብሎ ስለሚታመን ሁሉም የነፍስ ወከፍ ጥንቃቄ የሚያደርግበት ወቅት ነው፡፡ በጉራጌዎች እምነት መሠረት "መስቀል" ሁሉንም ነገር አዋቂ፣ ሰሚ፣ ተመልካችና ለእግዚአብሔር ቅርብ የሆነ አንዳች ዓይነት መለኮታዊ ኃይል ያለው ነው ተብሎ ከጥንት ጀምሮ ይታመናል፡፡

በመስቀል ወንዶች የእርድ ከብት በደጃቸው አርደው ወይም ከቅርብ ወዳጃቸው በጋራ አርደው ተከፋፍለው ሥጋ ይዘው ወደ ቤታቸው በሚሄዱበት ጊዜ ሴቶች ቤቱን የበዓል በዓል ሽታ ሰጥተውት ይጠብቋቸዋል፡፡ ዓመቱን ሙሉ ተሰቅለው የከረሙ የመስቀል በዓል መመገቢያ ባህላዊ እቃዎች ወርደው እና ተዘጋጅተው (ታጥበው፤ተወልውለው፤ታጥነው) አገልግሎት መስጠት የሚጀምሩት በዚህ ዕለት ነው፡፡

ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ቀናት ሁሉ በመስቀር ቀናቶች የየራሳቸው ሚናና መጠሪያ አላቸው፡፡

Ø መስከረም 13 እንቅልፍ ከልካይ ቀን ይባላል፡፡

v ምክንያቱም ሴቶች በቀጣዩ የዋናው በዓል ዋዜማ ዝግጅት እየተዋከቡ የሚያመሹበት፤ ልጆች ነገ በየደጃፉ የተከሏቸው ደመራዎች ስለሚለኩሱበት ሁኔታ፤ የሚገዛላቸው ልብስና ተገዝቶ የቀረበው ወይም የሚቀርበው የእርድ ከብት ለማየት ወይም ለመንከባከብ የሚጓጉበት፤ ይህንን ያላዘጋጀ አባት ደግሞ በሀሳብ ተጠምዶ ያለእንቅልፍ የሚያድርበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡

Ø መስከረም 14 ይፍት (ዋዜማ) ወይም የልጆች ደመራ ቀን ተብሎ ይጠራል::

  • • ሙሉ በሙሉ በእናቶች ወጪ የሚሸፈን የጎመን ክትፎ የሚበላበት፤ ሙስሊም የሆኑ ጎረቤቶች የሚጋበዙበት፤ የልጆች ደመራ የሚለኮስበትና ለዋናው በዓል አቀባበል የሚደረግበት ቀን ነው፡፡ በዚህ ምሽት በየቤቱ ደጃፍ የሚከበረው የደመራ በዓል ሥነ-ሥርዓት በሚፈፀምበት ጊዜ ደመራው በሚያመነጨው ብርሃን በየመንደሩ የሚከናወነው የወጣቶቹ ዘፈን፤ የሙየቶች ህብረ-ዝማሬ እንዲሁም በዚያ ምሽት በየመንደሩ የተለኮሱት ደመራዎች የሚያመነጩት የብርሀን ቀለም፣ ከደመራዎቹ ጭስ ጋር እየተቀላቀሉ ወደ ሰማይ ከፍ ብለው አየር ላይ የሚበታተኑት የእሳት ፍንጣቂዎች ለምሽቱ ልዩ ውበት በመስጠት የበዓሉን ሥነ-ሥርዓት ያደምቁታል፡፡ ይህንን ለሚታደም የምሽቱ እድሜ መራዘምን ያስመኛል፡፡

Ø መሰከረም 15 ቀን በመፅሀፍ ቅዱስ የኦሪትን ሥርዓት በተከተለ አግባብ በሚፈጸመው የእርድ ሥርዓት የሚከበረው በዓል "የጉራጌ መስቀር" ወይም "ወኸምያ/አርደማይ" ይባላል፡፡

Ø ቀጣዩ መስከረም 16 የአዋቂዎች ደመራ የሚበራበት ዕለት ሲሆን በአብዛኛው ሀይማኖታዊ ይዘት ይላበሳል፡፡

Ø መስከረም 17 ቀን ትልቁ በዓል ይባላል፡፡ መስከረም 15 (ረቡዕ ወይም አርብ ካልሆነ) የታረደው ሻኛ የሚቆረጥበት ቀን ስለሆነም የሻኛ ቀን ተብሎም ይጠራል፡፡ ከደመራ ማግስት በመሆኑም የከሠል ቀን እየተባለም ከሌሊቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአንድ አጥቢያ የሚተዳደሩ ዕድርተኞች ደመራ ወደ ተቃጠለበት ቦታ ሄደው በመሰብሰብ በአካባቢው የሚሰጠውን ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ቃለ-መሀላ ፈጽሞ አዲስ የአካባቢ ዳኛ የሚሾምበትና ባለፈው ዓመት ተሹሞ ሲያገለግል የነበረው ደግሞ ሹመቱን የሚያስረክብበት፤ አዲስ የአባልነት ጥያቄ የሚቀርብበትና ምዝግባ የሚካሔድበት ዕለት ነው፡፡ በየገበያውና በየአደባባዩ ባህላዊ የመስቀል ጨዋታም በዚሁ ቀን ተጀምሮ እስከ ጥቅምት 5 ቀን ድረስ ደምቆ ይቀጥላል፡፡

Ø መስከረም 18 ቀን ትንሹ በዓል ይባላል፡፡ የስንደዶ ቀን እየተባለም ልጃገረዶች መሶብና መሰል እቃዎች የሚሰሩበት ስንደዶ መልቀም የሚጀምሩበት ቀን ነው፡፡

በአጠቃላይ ስለ ጉራጌ መስቀል ብዙ ማለት የሚቻል ቢሆንም የበዓሉን ታሪካዊ ዳራ በጥልቀት ያጠኑ ምሁራን የተሻለ ትንታኔ የሚሰጡበት በመሆኑ በዚህ ማብቃት ግድ ይለኛል፡፡

በመጨረሻም በጉራጌ ማህበረሰብ በልዩ ሁኔታ የሚከበረው መስቀር በዓል ተወላጁ ከዘማድ አዝማድ ጋር ካለበት የትኛውም የሀገራችን ክፍል ተሰባስቦ ባህሉን ለሌሎች ኢትዮጵያዊያን ለማሳየት ጓደኞቹን ይዞ ወደ ቀየው ሲንቀሳቀስ እንደወትሮው ሁሉ ከቤተሰቡ በተጨማሪ የኢኮኖሚ ድጋፍ የሚሹት ወገኖቹን እንዲደግፍ፤ የተጣላን እንዲያስታርቅ እና የበደለውን ይቅር እንዲባባል፤ ታታሪነቱን እና ሰላም ወዳድነቱን ዛሬም በአርዓያ እንዲያስቀጥል አደራ እያልኩ በዚህ አጋጣሚ ዩኒቨርሲቲያችን የጀመረው የማህበረሰቡን ቱባ ባህል የመጠበቅ፣ የማጥናትና የማልማት፤ ከሀገራችን አልፎ ለዓለም ህብረተሰብ እሴቱን የማስተዋወቅ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በዚህ አጋጣሚ እየገለጽኩ በዓሉ የሰላም፣ የብሩህ ተስፋ፣ የበረከት እና የአንድነት እንዲሆን ለመላው ኢትዮጵያዊያን እመኛለሁ፡

የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ 13ኛ ዓመት አስመልክቶ “ የዓባይ ዘመን ትውልድ “ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የስነ-ጽሁፍ ፕሮግራም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

Read more ...

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት አባላት የዋቤ የንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ የፈረዝየ የአቮካዶ እርሻን እና የምርምር ጣቢያ የስራ እንቅስቃሴዎችን ጎበኙ።

Read more ...

በ2016 የትምህርት ዘመን ለማማካሻ ትምህርት (Remedial) ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡት ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ወደ ተቋሙ መግባት ጀምረዋል

Read more ...

Public Lecture has been held at Wolkite University

Read more ...

በ2015 ዓ.ም. በመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ኮሌጆችና የትምህርት ክፍሎች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ባለድርሻ አካላት እውቅና ተሰጠ

Read more ...

“የባህር በር ጥያቄ የፖለቲካ ወይስ የህልውና ጥያቄ ? “ በሚል ርዕስ ላይ ያተኮረ ሴሚናር በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

Read more ...

ዩኒቨርሲቲያችን በአገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የአቪዬሽን ኢኖቬሽን ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እያከናወነ ያለውን ተስፋ ሰጪ ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት የትምህርት ሚኒስቴር የሱፐርቪዢን ቡድን አሳሰበ

Read more ...

Announcement for Test Takers of National Graduate Admission Test (GAT)

Read more ...

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የካውንስል አባላት በዩኒቨርሲቲው የ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ተወያዩ

Read more ...

የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በመገምገም ላይ ይገኛሉ

Read more ...

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የጨቅላ ሕጻናት የእንክብካቤ ማዕከል እና የመምህራን መኖሪያ በሆነው አፓርታማ ግቢ ውስጥ የሚገኘው ሞዴል የማህበረሰብ መድሃኒት ቤት በይፋ ተመረቁ

Read more ...

በ2014 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ለመተግበር በዋቤ ችግኝ ጣቢያ የተዘጋጁት ችግኞችን አስመልክቶ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የስፔሻሊቲ የትምህርት ፕሮግራሞችን መስጠት ጀመረ

Read more ...

We have 536 guests and no members online

Wolkite University, P.O.Box 07, Wolkite, Guragie Zone, SNNPR, Ethiopia | +251-113-220042 | pird@wku.edu.et/president@wku.edu.et

Copyright © 2024. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT