የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የ1443ኛው የዒድ-አል አረፋ በዓል ከተማሪዎች ጋር አከበሩ። በፕሮግራሙ የተገኙት የዩኒቨርሰቲው ፕሬዝዳንት ለተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክ ተማሪዎች በግቢ ቆይታቸው አብሮነትን፣ ፍቅርና መተሳሰብን እንዲያዳብሩ አደራ ብለዋል። አያይዘውም ሀገራችን እየገጠሟት ያሉ ፈተናዎች ለመሻገር ከመቼም ጊዜ በላይ አብረን መቆም እንዳለብን አንስተው ተማሪዎች የሰላም አምባሰደር በሆነው ዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው እያሳዩት ያለው ሰላም ወዳድነት እንዲያጠናክሩ አደራ በማለት በድጋሚ መልካም በዓል ተመኝተዋል።