በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በኩል የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን የፈረሙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል ሲሆኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኩል ስምምነቱ የተፈረመው በፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ሲሆን ፕሮፈሰር ጣሰው ወልደሃናን በመወከል ፕሮፌሰር አታላይ አየለ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በስምምነቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡ በስምምነቱ ላይ እንደተገለጸው በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ውስጥ Broad band seismic station ለማቋቋም ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ የተስማሙ ሲሆን በዚሁ መሰረት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱ ለ5 አመት ጸንቶ እንደሚቆይ ከሰነዱ ላይ ለመረዳት ተችሏል፡፡